From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጫላ (Tesfaye Chala)
|
|
፭ (5)
|
ይታይ (Yetay)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፬ (4)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Chala)
|
|
"መምህር ፡ ሆይ ፡ ይህች ፡ ሴት ፡ ስታመነዝር ፡ ተገኝታ ፡ ተያዘች
ሙሴም ፡ እንደዚህ ፡ ያሉት ፡ እንዲወገሩ ፡ በህግ ፡ አዟል
አንተስ ፡ ስለእርሷ ፡ ምን ፡ ትላለህ"
ባያድላት ፡ እንጂ ፡ ቀኑ ፡ ቢከፋባት
እንደአንተዉ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ወግ ፡ ያናፈቃት
እንደአንቺው ፡ እንደእኔ ፡ ወግ ፡ እየናፈቃት
ተኳኩላ ፡ ወጣች ፡ ፀሐይ ፡ ስታልቅባት
ሳያት ፡ ሆዴ ፡ ባባ ፡ እንዴት ፡ ልታደጋት
ምነው ፡ እንደህልሟ ፡ በክብር ፡ በተዳረች
ለጠፊ ፡ ለአላፊ ፡ እንቃ??? ፡ አካሏን ፡ ሸጠች
ኀጢአት ፡ የሌለበት ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ ይፍረድባት
እኔ ፡ ሲታየኝ ፡ ይህች ፡ ሴት ፡ ቀን ፡ አላት
ምህረት ፡ ወረደ ፡ ከላይ (ከላይ (፫x)) ፡ አዳኟ ፡ ይቅር ፡ አላት
ኀጢአት ፡ ያልተገኘበት ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ ሚፈርድባት
ከእንግዲስ ፡ በቃው ፡ በለው ፡ አውጥቶ ፡ ሰው ፡ ለጣለው
ለተታለው ፡ ለዚያው ፡ ሰው ፡ እግዚአብሔር ፡ እቅድ ፡ አለው
ቆሻሻውን ፡ ይጠርግና ፡ እህህ ፡ ሸልሞ ፡ ያቆመዋል
ሰው ፡ አበቃ ፡ ባለ ፡ ቀን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይጀምራል (፪x)
ዙሪያ ፡ ሲሰካ??? ፡ ቀን ፡ ሲጨላልም
አካሏን ፡ ሸጣ ፡ ውላ ፡ ብታድር
ለአፍታሪክ ፡ ??? ፡ ብቻ ፡ አትፈልግም
እንደሰው ፡ ሃሳብ ፡ እስቲ ፡ ዘመርላት???
ስም ፡ ተለጥፎባት ፡ ብትከሰስ
ሁሉን ፡ የሚያየው ፡ ዳኛ ፡ ጋር ፡ ስትደርስ
አትፍሪ ፡ ብሎ ፡ ምህረት ፡ ለገሳት
ሰው ፡ ያጨለመውን ፡ ቀን ፡ አወጣላት
(ያነሳል) ፡ ኀጢአተኛውን ፡ ሰው
(ያነሳል) ፡ ሸልሞ ፡ ሊያቆመው
(ያነሳል) ፡ ለክብሩ ፡ መግለጫ
(ያነሳል) ፡ ክብር ፡ እቃ ፡ ሊያደርገው
(ያነሳል) ፡ የቆሸሸውን ፡ ማንጻት
(ያነሳል) ፡ ማንጻት ፡ ነው ፡ ልማዱ
(ያነሳል) ፡ ቀን ፡ አለ ፡ ቀን ፡ አለው
(ያነሳል) ፡ በኀጢአት ፡ ለተጐዱ (፬x)
|