From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጫላ (Tesfaye Chala)
|
|
፭ (5)
|
ይታይ (Yetay)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ (10)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Chala)
|
|
ለአንዱ ፡ ሲነጋለት ፡ ለአንዱ ፡ ሲመሽበት
በጠራራው ፡ ፀሐይ ፡ ቀን ፡ ሲጨልምበት
የሰው ፡ ማንነቱ ፡ በገንዘብ ፡ ሲለካ
ሃያል ፡ በጉልበቱ ፡ በኃይሉ ፡ ሲመካ
በገንዘብ ፡ ታፍናለት ፡ ስትደበቅ
የታመነ ፡ ወድቆ ፡ የቀጠፈ ፡ ሲደርቅ
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጉዳይ ፡ ፍርድ ፡ ጐዶሎ ፡ ነው
በዘመኔ ፡ ታዘብኩ ፡ በዐይኖቼ ፡ ይህን ፡ አየሁ
አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ
ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው
ለመበለቷ ፡ በቅን ፡ ይፈርዳል
የሃዘንተኛውን ፡ እንባ ፡ ያብሳል
ለተገፋው ፡ ሰው ፡ ለምስኪን ፡ አዛኝ
የተሰበረውን ፡ በቃል ፡ ጠጋኝ
ይኼ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የተመማነኩበት
ይኼ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት (፪x)
ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ ፡ ልብ ፡ ያለው ፡ ይመከር
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር (፪x)
እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው
አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ
ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው
ያጣ ፡ እያገኘ ፡ ያገኘም ፡ እያጣ
የወጣም ፡ ወረደ ፡ የወረደም ፡ ወጣ
እንደጊዜው ፡ ሆኖ ፡ ሕይወት ፡ ሲቀያየር
ሃያል ፡ ጉልበት ፡ አጥሮት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲበቀል
በሚያልፈው ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ እንዴት ፡ ተስፋ ፡ ይጣላል
ሸመቆ ፡ አይደል ፡ አንድቀን ፡ ይከዳል
የልብ ፡ ጓደኛህ ፡ እስከሞት ፡ የሚወድ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ
አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ
ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው
ይኼ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የተመማነኩበት
ይኼ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት (፪x)
ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ ፡ ልብ ፡ ያለው ፡ ይመከር
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር (፪x)
እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)
|