በማለዳ (Bemaleda) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 5.jpeg


(5)

ይታይ
(Yetay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

 
ያ ፡ ሌሊት ፡ ትዝ ፡ አለኝ (፬x)
እንዴት ፡ ይታለፋል ፡ እያልኩ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት
በምድር ፡ መፈጠሬን ፡ የተራገምኩበት
ያ ፡ ሌሊት ፡ ትዝ ፡ አለኝ (፪x)
አንተ ፡ ስትመጣ ፡ በችግሬ ፡ ላይ
ጩኸቴን ፡ ሰምተህ ፡ ስትወርድ ፡ ከላይ
የማይቻለውን ፡ ስትችል ፡ እያየሁ
ከነፍሴ ፡ ዜማ ፡ ምሥጋና ፡ ኢሄው
(፪x)

አዝ፦ በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በምሽትም ፡ ደግሞ ፡ በሌሊትም
አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዲስ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ይቅረብልህ ፡ ገና (፪x)

የአምላኬ ፡ ጉብኝት ፡ ሁልጊዜ??? ፡ ደረሰ
የምስኪኑን ፡ ሰው ፡ እንባው ፡ ታበሰ
ቆሞ ፡ አደባባይ ፡ ቃኘ ፡ በገና
ስሙት ፡ ሲዘምር ፡ አዲስ ፡ ምሥጋና (፪x)

አዝ፦ በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በምሽትም ፡ ደግሞ ፡ በሌሊትም
አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዲስ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ይቅረብልህ ፡ ገና (፪x)

ያ ፡ ሌሊት ፡ ትዝ ፡ አለኝ (፬x)
የጨለማው ፡ ብርታት ፡ የማይነጋ ፡ መስሎኝ
የጐኔን ፡ እንዳላይ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከልሎኝ
ያ ፡ ሌሊት ፡ ትዝ ፡ አለኝ (፬x)
አለቀ ፡ ብላ ፡ ነፍሴ ፡ ስትፈራ
የደረስክልኝ ፡ ስምህን ፡ ስጠራ
ጨለማውን ፡ ቀን ፡ ቀን ፡ ያደረግከው
ከነፍሴ ፡ ዜማ ፡ ምሥጋና ፡ ይሄው
(፪x)

አዝ፦ በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በምሽትም ፡ ደግሞ ፡ በሌሊትም
አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዲስ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ይቅረብልህ ፡ ገና (፪x)