From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጫላ (Tesfaye Chala)
|
|
፭ (5)
|
ይታይ (Yetay)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፱ (9)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Chala)
|
|
አንደበት ፡ ኖሯቸው ፡ ምድርና ፡ ሰማይ
ምነው ፡ ቢናገሩ ፡ እንደሌለው ፡ መሳይ (፫x)
እኔስ ፡ በዚች ፡ ቃሌ ፡ በትንሿ ፡ አንደበት
አልወጣልህ ፡ አለኝ ፡ ዘምሬ ፡ የእርሱን ፡ ምህረት
ያምላኬን ፡ በጐነት (አሃሃ) ፡ የአምላኬን ፡ ቸርነት
ጥሩ ፡ ቃል ፡ ተመርጦ ፡ ዜማ ፡ ቢደረደር
በመልካም ፡ አዋቂ ፡ አምሮ ፡ ቢቀናበር
ልሳን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ለአፍታ ፡ ሳያባራ
አይበቃም ፡ ቢዘመር ፡ ስለእርሱ ፡ ቢወራ (፪x)
አዝ፦ (አሃሃ) ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፤ (አሃሃ) ፡ መለኪያ ፡ የለውም
(አሃሃ) ፡ ፍጥረት ፡ ይራመዳል ፤ (አሃሃ) ፡ እርሱ ፡ እንደሚለው
(አሃሃ) ፡ ይገድላል ፡ ያድናል ፤ (አሃሃ) ፡ ይሾማል ፡ ይሽራል
(አሃሃ) ፡ ዐይኖቹን ፡ እይታ ፤ (አሃሃ) ፡ ማን ፡ ሸሽቶ ፡ ይሰወራል
ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
አስፈሪው ፡ ማዕበል ፡ ወጀብ ፡ ታዘዘለት
ተራራው ፡ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ አለለት
ብቻውን ፡ ኤልሻዳይ ፡ በሃይል ፡ ይገዛል
ቢወድም ፡ ባይወድም ፡ ፍጥረት ፡ ይታዘዛል (፪x)
ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
check this section again
አጥቢያ ፡ ኮከብ ፡ ቆመው ፡ ፊቱ ፡ ሲዘምሩ
ሰማያት ፡ ሲሰግዱ ፡ ሲሞሉ ፡ በክብሩ (፫x)
መስፈሪያም ፡ ሲለካ ፡ ዙሪያዋን ፡ ሲገምት
ማን ፡ ነበር ፡ ያገዘው ፡ ምድርን ፡ ሲመሰርት (፫x)
በአደባባዮች ፡ ላይ ፡ ክህደት ፡ ሲዘመር
ያወቀ ፡ ሲመስለው ፡ ሰው ፡ ብዙ ፡ ሲናገር
የለም ፡ ያሉት ፡ ሄዱ ፡ ከነኮተታቸው
የእኛ ፡ አምላክ ፡ ግን ፡ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ ይኸው (፪x)
አዝ፦ (አሃሃ) ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፤ (አሃሃ) ፡ መለኪያ ፡ የለውም
(አሃሃ) ፡ ፍጥረት ፡ ይራመዳል ፤ (አሃሃ) ፡ እርሱ ፡ እንደሚለው
(አሃሃ) ፡ ይገድላል ፡ ያድናል ፤ (አሃሃ) ፡ ይሾማል ፡ ይሽራል
(አሃሃ) ፡ ዐይኖቹን ፡ እይታ ፤ (አሃሃ) ፡ ማን ፡ ሸሽቶ ፡ ይሰወራል
ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው
ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው
|