From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጫላ (Tesfaye Chala)
|
|
፭ (5)
|
ይታይ (Yetay)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Chala)
|
|
የገባልኝ ፡ ኪዳን ፡ ልቤን ፡ እያስንሳው
ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ (፪x)
ከተሰቀለበት ፡ በገናዬን ፡ ቃኘሁ
በአድደባባዮቹ ፡ እንዳምነው ፡ እንዳከብረው
ሞኝ ፡ ነው ፡ ጠላቴ ፡ ይህንን ፡ ዘነጋ
ጌታ ፡ ሳይለው ፡ ቀኔ ፡ እንደማይዘጋ
አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና
ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና
በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማህሌት ፡ እቆማለሁ
መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ
ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
በሞትና ፡ በእኔ ፡ መሃል ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ
በጭንቅ ፡ ቀን ፡ የሚረዳ ፡ የሚያግዝ ፡ ጠፍቶ
ዐይኖቼን ፡ ወደ ፡ ተራሮ ፡ እንኳን ፡ ባነሳ
እያሞካሸ ፡ የጠራኝ ፡ ወዳጄን ፡ ልረሳ
ቃሉን ፡ ልኮልኝ ፡ ከሰማይ ፡ ሃይሌን ፡ ያደሰው (ኦሆ)
ውበት ፡ የሰጠው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ለፈራረሰው (ኦሆ)
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ መኖሪያ (አሃ)
ልዘምር ፡ ሳላናጋግር ፡ ሳልሰማ ፡ ዙሪያ (ኦሆ)
አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና
ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና
በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማህሌት ፡ እቆማለሁ
መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ
ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
የገባልኝ ፡ ኪዳን ፡ ልቤን ፡ እያስንሳው
ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ
ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ እያለኝ
ቃል ፡ አለኝ ፡ ከሰማይ ፡ ኪዳን ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር
ተስፋዬን ፡ አስቦ ፡ ሁሌ ፡ ልቤ ፡ ተረጋጋ
ሃሳቡ ፡ ሳይሞላ ፡ ጠላቴ ፡ ሲሸበር
ምሥጋና ፡ እና ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ በእኔ ፡ ሰፈር
አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና
ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና
በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማለት ፡ እቆማለሁ
መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ
ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ
የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ
|