ይወደኛል (Yewedegnal) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 4.jpg


(4)

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ
(Yebelay Neh Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

 
አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x)

ነፍሱን ፡ የሰጠው ፡ ስለእኔ ፡ የታደገኝ ፡ ከኩነኔ
ምህረቱን ፡ ያበዛልኝ ፡ የቆመልኝም ፡ ከጐኔ
ነፍሴ ፡ ታምናው ፡ ረክታለች ፡ በጸጋው ፡ ብዛት ፡ ቆማለች
ያንን ፡ አስፈሪ ፡ ጨለማ ፡ ከአምላኳ ፡ ጋር ፡ ተሻግራለች
ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ሲሰቃይ ፡ እንደሚወደኝ ፡ ገብቶኛል
ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል
ይመቸኛል (፬x)

አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x)


የፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ ሲገባኝ ፡ ልቤን ፡ ሰጠሁ ፡ እንዲገዛኝ
ይንገሥብኝ ፡ ወድጃለሁ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ
ዋላ ፡ ውሃን ፡ እንደምትሻ ፡ እኔም ፡ ዘወትር ፡ እጠማዋለሁ
በነፍሴ ፡ ወደማደሪያው ፡ ወደ ፡ ፡ እርሱ ፡ እገሰግሳለሁ
የሚለየኝ ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ አስሮኛል
ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል
ይመቸኛል (፬x)

አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x)