የሚያኮራ ፡ ጌታ (Yemiyakora Gieta) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 4.jpg


(4)

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ
(Yebelay Neh Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

"ከቶ ፡ አይቸኩልም ፡ ዘግይቶ ፡ ይነሳል
ግን ፡ ማንም ፡ አይቀድመው ፡ ፈጥኖ ፡ ይደርሳል
በምድረ ፡ በዳ ፡ ምንጭ ፡ የሚያፈልቀው
ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ የምናመልከው
አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ንቃ ፡ ተነሳ
ክርስቶስ ፡ ከላይ ፡ ያበራልሃል
ሃይል ፡ ለሌለው ፡ ሃይል ፡ ይጨምራል
የደከመው ፡ መደገፍያ"

አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል
የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል
ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ
ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x)

በእሳቱ ፡ ውስጥ ፡ አለፍኩ ፡ አላቃጠለኝም
በወንዙ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ አላሰጠመኝም
ምህረቱ ፡ እንደጋሻ ፡ ሆኖ ፡ እየከለለኝ
ጠላቴ ፡ ሞቷል ፡ ሲል ፡ በሕይወት ፡ አለሁኝ

አዲሱን ፡ ዝማሬ ፡ ይዤ ፡ ወጥችሃለሁ
የጠላቴን ፡ መንደር ፡ አሸብረዋለሁ
አምላኬ ፡ እንደንስር ፡ ሃይሌን ፡ አድሶታል
ስሙን ፡ እየጠራሁ ፡ ቀንበር ፡ ይሰበራል

አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል
የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል
ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ
ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x)

ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ ፡ ቆሞ ፡ ሲያስጨንቀኝ
ሰራዊት ፡ እሁአላ ፡ ተግቶ ፡ ሲከተለኝ
እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ አምላኬን ፡ ጠራሁኝ
ሰመጠ ፡ ፈርዖን ፡ በዐይኖቼ ፡ እያየሁኝ

በተዐምር ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ የሚያኖረኝ
ስንትን ፡ አሳልፎ ፡ ቅጥሩን ፡ አዘለለኝ
ባሕር ፡ ተከፍሎልኝ ፡ በድል ፡ ተሻግሬ
አልጠገብኩም ፡ ገና ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሬ

አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል
የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል
ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ
ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x)