From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ መቃብሬን ፡ ከፍቶ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ማነው ፡ የሚቃወም
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ማነው ፡ የሚከሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላይ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ክፉውን ፡ አልፈራ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
አዝ:- ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሃ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ ያደገው ፡ ኦሆ (፪x)
በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ፊት ፡ ስፍራ ፡ የሌለው ፡ ሰው
ሁሉም ፡ ከደጃፉ ፡ አውጥቶ ፡ የጣለው
ይሄ ፡ ደካማ ፡ ሰው ፡ በአምላክ ፡ ተጐበኘ
በጻድቃን ፡ ጉባዔ ፡ ሲዘምር ፡ ተገኝ
አትሉም ፡ ወይ ፡ ታዲያ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ምስኪኑን ፡ ከአምድ ፡ ላይ ፡ አንስቶ ፡ አከበረው (፪x)
ያልቀመሰ ፡ ማነው ፡ ምህረት ፡ ቸርነቱን (፪x)
እስቲ ፡ በምሥጋና ፡ እንሙላው ፡ መቅደሱን (፪x)
አዝ:- ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሃ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ ያደገው ፡ ኦሆ (፪x)
የሜበሉን ፡ ብርታት ፡ ወጀቡን ፡ አይቼ (፪x)
ወየሁ ፡ ጠፋሁ ፡ በቃ ፡ እያልኩኝ ፡ ፈርቼ (፪x)
ሞት ፡ እያጣጣረኝ ፡ አምላኬን ፡ ጠራሁኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ ጠራሁኝ
ወጥመድ ፡ ተሰበረ ፡ ከሞት ፡ አመለጥኩኝ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ መቃብሬን ፡ ከፍቶ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ማነው ፡ የሚቃወም
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ማነው ፡ የሚከሰኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላይ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ክፉውን ፡ አልፈራ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
አዝ:- ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሃ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ ያደገው ፡ ኦሆ (፪x)
ሥሙን ፡ ተጣርቼ ፡ ከቶ ፡ አፍሬ ፡ አላውቅም (፪x)
ጠላት ፡ ቢፎክርም ፡ ልቤ ፡ አይደነግጥም (፪x)
አምላኬን ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ (፪x)
ስሙን ፡ እያወደስኩ ፡ ገና ፡ እኖራለሁ (፪x)
አዝ:- ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሃ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ ያደገው ፡ ኦሆ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሃ (፪x)
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ ያደገው ፡ ኦሆ (፮x)
|