ኢየሱስ (Eyesus) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 4.jpg


(4)

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ
(Yebelay Neh Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

ቀኑ ፡ እንዴት ፡ ይገፋል ፡ ያለመጨነቅ
በሃሳብ ፡ ማጥ ፡ ውስጥ ፡ መማቀቅ (፪x)
ሳይሞላለት ፡ ዛሬን ፡ ነገን ፡ ሲፍጨረጨር
በሥጋት ፡ ብዛት ፡ ሲወጠር (፪x)
የሰው ፡ ሕይወት ፡ በምድር ፡ ሰልፉ ፡ እንዴት ፡ ብርቱ ፡ ነው
ማነው ፡ ከዚህ ፡ መዓት ፡ የሚገላግለው

አዝ:- የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ ያለው
መፍትሄው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ኢየሱስ (፲፪x)
የሁሉን ፡ ሚስጥር ፡ ቁልፉን ፡ ይዘሃል
በአሰራርህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው
እንዲህ ፡ አታድርግ ፡ የሚልህ ፡ ማነው

ሕይወትም ፡ በድንገት ፡ ሲለብስ ፡ ደመና
ደጅ ፡ ሲወጣ ፡ ገበና (፪x)
ያላሰቡት ፡ ሲደርስ ፡ ያሰቡት ፡ ሳይሞላ
ሰው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሲጣላ (፪x)
የሰው ፡ ሕይወት ፡ በምድር ፡ ሰልፉ ፡ እንዴት ፡ ብርቱ ፡ ነው
ማነው ፡ ከዚህ ፡ መዓት ፡ የሚገላግለው

አዝ:- የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ ያለው
መፍትሄው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ኢየሱስ (፲፪x)
የሁሉን ፡ ሚስጥር ፡ ቁልፉን ፡ ይዘሃል
በአሰራርህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው
እንዲህ ፡ አታድርግ ፡ የሚልህ ፡ ማነው