From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- በማዕበሉ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
በወጀቡ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)
ያላሰብኩት ፡ ቢሆን ፡ አሃሃሃ ፡ ነገር ፡ ቢቀያየር ፡ ኦሆሆሆ
ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ አሃሃሃ ፡ ሸንበቆው ፡ ቢሰበር ፡ ኦሆሆሆ
ዐይን ፡ የሚጣልበት ፡ አሃሃሃ ፡ አንድ ፡ እንኳን ፡ ቢጠፋ ፡ ኦሆሆሆ
ወጀቡ ፡ በርትቶ ፡ አሃሃሃ ፡ ለነገ ፡ ቢከፋ ፡ ኦሆሆሆ
ድምጹን ፡ ሳልሰማ ፡ የማዕበሉን
ሳላይ ፡ ያን ፡ ሃይል ፡ የንፋሱን
በሙሉ ፡ ልቤ ፡ ጠራሃለው
ለአንተ ፡ የማይሰግድ ፡ የማይቆም ፡ ማነው
አዝ:- በማዕበሉ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
በወጀቡ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ ፡ አሃሃሃ ፡ ቆሞ ፡ ሲያስጨንቅኝ ፡ ኦሆሆሆ
ፈርንም ፡ ከሁአላ ፡ አሃሃሃ ፡ ሊመጣ ፡ ቢውጠኝ ፡ ኦሆሆሆ
የማመልክህ ፡ አምላክ ፡ አሃሃሃ ፡ ወዴት ፡ ነህ ፡ እላለሁ ፡ ኦሆሆሆ
በቃልህ ፡ እኔ ፡ ቆሜ ፡ አሃሃሃ ፡ ስምህን ፡ እጠራዋለሁ ፡ ኦሆሆሆ
ጩኀቴን ፡ ሰምተህ ፡ ከሰማያት
እራርተህልኝ ፡ እንደአባት
መንጥቀህ ፡ ስንቴ ፡ አውጥተኀኛል
የአምናው ፡ ለነገ ፡ እምነት ፡ ሆኖኛል
አዝ:- በማዕበሉ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
በወጀቡ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)
|