From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ መከራዬን ፡ አስረሳኝ
በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ እራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይበዛል ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ባከብረው
ማንም ፡ የማይመስለው ፡ ወዳጅ ፡ አግኝቻለሁ (፬x)
አሃ ፡ የጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ አሃ ፡ አይ ፡ ማስፈራራቱ
አሃ ፡ ከንቱ ፡ ሆኖ ፡ ቀረ ፡ አሃ ፡ ቀደመች ፡ ምህረቱ
አሃ ፡ ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ አሃ ፡ በደመና ፡ መራኝ
አሃ ፡ እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ አምላኬ ፡ ከረዳኝ
እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ከረዳኝ
አዝ:- አደረገልኝ ፡ ተዐምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ ሃሃ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
ዘይት ፡ ከማሰሮ ፡ ከማድጋው ፡ አልቆ
ተስፋዬ ፡ ተሰብሮ ፡ ተሰባብሮ ፡ ደቆ
ስሙን ፡ ተጣርቼ ፡ የልቤን ፡ ስነግረው
እፌን ፡ ሞልቶ ፡ በሳቅ ፡ ሕይወቴን ፡ አዳነው
የአምናው ፡ ችግር ፡ ሄደ ፡ ማድጋው ፡ ሙሉ ፡ ነው
ከእርሴ ፡ ተርፌ ፡ አለኝ ፡ የምሰጠው
የተዐምራት ፡ አምላክ ፡ ተዐምር ፡ አድርጐልኛል
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይስማው ፡ ነገር ፡ ተገልብጧል
አዝ:- አደረገልኝ ፡ ተዐምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ ሃሃ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
አሃሃ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ላምጣ ፡ አሃሃ ፡ ላክብረው ፡ ሳልቆጥብ
አሃሃ ፡ እግሮቼም ፡ ይዝለሉ ፡ በፊቱ ፡ ላሸብሽብ
አሃሃ ፡ ክብሬን ፡ ብጥልለት ፡ አሃሃ ፡ የሚንቀኝ ፡ ማነው
አሃሃ ፡ ያደረገልኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
አሃሃ ፡ የተሰራልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
ሰማይ ፡ ጥርት ፡ አለ ፡ ደመናውም ፡ ጠፋ
የችግሩ ፡ ብርታት ፡ በፊቴ ፡ ለቆ ፡ ጠፋ
የነበረው ፡ ሄደ ፡ ያለውም ፡ አለቀ
ውኃ ፡ ሳይኖርበት ፡ ሸለቆው ፡ ደረቀ
ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ንፋስም ፡ ሳይነፍስ
ዝናባትን ፡ አዞ ፡ ምድርን ፡ ሲያረሰርስ
የጠላቴን ፡ እቅድ ፡ እያፈረሰልኝ
ድል ፡ በድል ፡ ላይ ፡ እመድኩ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
አዝ:- አደረገልኝ ፡ ተዐምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ ሃሃ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
|