ይብዛለት ፡ ምሥጋና (Yebzalet Mesgana) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

ይሁን ፡ እንጂ ፡ ይብዛለት ፡ ምሥጋና
ሳላቋርጥ ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና
አይደክመኝም ፡ ሁሌ ፡ አመልከዋለሁ
ለሕይወቴ ፡ ትርጉሟ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

ተሰጥቼ ፡ አመልካለሁ ፡ በፈቃዴ ፡ አመልካለሁ
በመንፈሴ ፡ አመልካለሁ ፡ በእውነትም ፡ አመልካለሁ
በማለዳም ፡ አመልካለሁ ፡ በቀትርም ፡ አመልካለሁ
በምሽትም ፡ አመልካለሁ ፡ በሌሊትም ፡ አመልካለሁ
በዝማሬም ፡ አመልካለሁ ፡ በሽብሸባም ፡ አመልካለሁ
በደስታም ፡ አመልካለሁ ፡ በዕልልታም ፡ አመልካለሁ

አሞጋግሼው ፡ መቼ ፡ ጨረስኩና
ገና ፡ አልጠገብኩም ፡ አቅርቤ ፡ ምሥጋና
ባማረ ፡ ዜማ ፡ እቀኝለታለሁ
በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ማልጄ ፡ እነሳለሁ
አለብኝ ፡ ውለታው (፰x)

እንዴት (፬x) ፡ እረሳለሁ
እንዴት (፬x) ፡ እረሳለሁ
ኧረ ፡ እንዴት (፬x) ፡ ዝም ፡ እላለሁ
እንዴት (፬x) ፡ ዝም ፡ እላለሁ
የተደረገልኝ ፡ ምህረት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የተደረገልኝ ፡ ቸርነት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የተደረገልኝ ፡ በጐነት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው

ገና ፡ ከፍጥረቴ ፡ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ነበርኩ (፪x)
ምህረት ፡ ተደርጐልኝ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ታረኩ (፪x)
ያጐበጠኝ ፡ ቀንበር ፡ ወደቀ ፡ ከላዬ (፪x)
አምሮብኝ ፡ ብታዩኝ ፡ በአምላኬ ፡ ዛሬ ፡ ቀና ፡ ብዬ (፪x)

በኃጥያቴ ፡ ሙታን ፡ እያለሁ
ከእግዚአብሔር ፡ ምረት ፡ ተቀብያለሁ
ለሆነው ፡ ነገር ፡ ምን ፡ እከፍላለሁ
ቀንና ፡ ሌሊት ፡ እዘምራለሁ (፪x)

አሞጋግሼው ፡ መቼ ፡ ጨረስኩና
ገና ፡ አልጠገብኩም ፡ አቅርቤ ፡ ምሥጋና
ባማረ ፡ ዜማ ፡ እቀኝለታለሁ
በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ማልጄ ፡ እነሳለሁ
አለብኝ ፡ ውለታው (፰x)

ተሰጥቼ ፡ አመልካለሁ ፡ በፈቃዴ ፡ አመልካለሁ
በመንፈሴ ፡ አመልካለሁ ፡ በእውነትም ፡ አመልካለሁ
በማለዳም ፡ አመልካለሁ ፡ በቀትርም ፡ አመልካለሁ
በምሽትም ፡ አመልካለሁ ፡ በሌሊትም ፡ አመልካለሁ
በዝማሬም ፡ አመልካለሁ ፡ በሽብሸባም ፡ አመልካለሁ
በደስታም ፡ አመልካለሁ ፡ በዕልልታም ፡ አመልካለሁ