From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x)
ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ሲሸምቅ
የወደኩ ፡ መስሎት ፡ በእኔ ፡ ሊስቅ
ነጋሪት ፡ ሲመታ ፡ ሲያስመታ
እምነቴን ፡ ጉልበቴን ፡ ሊፈታ
ቀና ፡ ብዬ ፡ ባላይ ፡ ኖሮ ፡ ዓይኖቸን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አንስቼ
በጠፋሁ ፡ ነበር ፡ አስካሁን ፡ በሰልፉ ፡ ብዛት ፡ ፈርቼ
ደካማን ፡ የምትረዳ ፡ አምላክ ፡ አኔን ፡ ደርሰህ ፡ እረዳኸኝ
መከራዬን ፡ አሳለፍከው ፡ በኮረብታው ፡ ላይ ፡ አቆምከኝ
አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x)
ጠንክሮ ፡ ብዙ ፡ የፈተነኝ ፡ የማይገፋ ፡ የመሰለኝ
ወደቀ ፡ እንደ ፡ ቀላል ፡ ዕቃ ፡ ሰማሁት ፡ ድንፋታው ፡ ሲያበቃ
ቀና ፡ ብዬ ፡ ስመለከት ፡ ከመከራዬ ፡ ቀን ፡ በላይ
ለካስ ፡ ጌታ ፡ አስቦልኝ ፡ ቤቴን ፡ በበረከት ፡ ሊሞላ
ሸሸገኝ ፡ ከጉያው ፡ ገባሁ ፡ ከጥላው ፡ ሥር ፡ አሳደረኝ
እዘምራለሁ ፡ ለሥሙ ፡ በቤቱ ፡ ስለተመቸኝ
አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x)
ኃይሌ ፡ ነው ፡ እታመነዋለሁ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ እደገፈዋለሁ
ሞገሴ ፡ የማያሳፍረኝ ፡ በፀጋው ፡ የሚደጋግፈኝ
መከታዬ ፡ ነው ፡ ጋሻዬ ፡ ሥሙን ፡ በእውነት ፡ እጠራዋለሁ
ስንቱን ፡ ሸለቆ ፡ ተራራ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ አልፌአለሁ
ከጐኔ ፡ የሚቆም ፡ ዘለዓለም ፡ እንዴ ፡ እንኳን ፡ አላሳፈረኝ
በአምላኬ ፡ ቀን ፡ ወጥቶልኛል ፡ እንግዲህ ፡ ማን ፡ ሊቃወመኝ
አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፰x)
|