ምህረት ፡ ሲበዛልኝ (Meheret Sibezalegn) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

እጆቸን ፡ ዘርግቼ ፡ ጌታ ፡ እጆቸን ፡ ዘርግቼ ፡ አሃሃ
አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ
ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ ጌታ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ አሃሃ
ክብር ፡ አሰጥሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ አሰጥሃለሁ

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ

በበዛው ፡ በደል ፡ ኃጢአቴ ፡ ላይ
ምህረትህ ፡ ገብቶ ፡ ባይከልለኝ
ቸርነትህም ፡ ሞገስ ፡ ሆኖ
በሄድኩበት ፡ መንገድ ፡ ባይረዳኝ
ምን ፡ ልሆን ፡ ነበር ፡ ምን ፡ ሊውጠኝ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ እንዴት ፡ ላልፈው
ጌታ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ቸር ፡ ነህና
ለቅሶዬን ፡ በደስታ ፡ ለወጥከው

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ

እጆቸን ፡ ዘርግቼ ፡ ጌታ ፡ እጆቸን ፡ ዘርግቼ ፡ አሃሃ
አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ
ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ ጌታ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ አሃሃ
ክብር ፡ አሰጥሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ አሰጥሃለሁ

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ

የአምላኩ ፡ ምህረት ፡ የበዛለት ፡ በጌታው ፡ ሞገስ ፡ ያማረበት
ቸርነቱ ፡ የተከተለው ፡ እጆቹን ፡ ይዞ ፡ ያሻገረው
ጠላቱን ፡ ከእግሩ ፡ የጣለለት ፡ መንገዱ ፡ ቀና ፡ የሆነለት
በፀጋው ፡ ብዛት ፡ የደገፈው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ደስ ፡ የሚለው

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ

በኖ ፡ እያየሁት ፡ እንደ ፡ አቧራ ፡ ጠላቴ ፡ ጠፋ ፡ ከመንገዴ
ኃይል ፡ አገኘሁ ፡ እንደገና ፡ ጠነከረልኝ ፡ ጉልበት ፡ ክንዴ
ተሻገርኩ ፡ ባሕሩን ፡ ተላለፍኩት ፡ አምላኬን ፡ በዓይኖቼ ፡ አየሁት
ለዚህ ፡ ነው ፡ ቆሜ ፡ የምዘምረው ፡ ሌላ ፡ ስላጣሁ ፡ የማደርገው

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኦሆ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ

የአምላኩ ፡ ምህረት ፡ የበዛለት ፡ በጌታው ፡ ሞገስ ፡ ያማረበት
ቸርነቱ ፡ የተከተለው ፡ እጆቹን ፡ ይዞ ፡ ያሻገረው
ጠላቱን ፡ ከእግሩ ፡ የጣለለት ፡ መንገዱ ፡ ቀና ፡ የሆነለት
በፀጋው ፡ ብዛት ፡ የደገፈው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ደስ ፡ የሚለው

አዝ፦ ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተወጣሁት ፡ ያን ፡ ተራራ ፡ አሃ
አልደከመኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኦሆ
ምህረትህ ፡ ሲበዛልኝ ፡ አሃ
ቸርነትህ ፡ ሲደግፈኝ ፡ ኦሆ
ተሻገርኩት ፡ ያን ፡ ሸለቆ ፡ ኦሆ
አየሁ ፡ ጠላት ፡ ፊቴ ፡ ወድቆ ፡ ኦሆ