ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (Keber Ante Becha) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

ኃያላን ፡ ከምድር ፡ ተሰብረው ፡ ሲወድቁ
በራሳችው ፡ በትር ፡ እራሳቸው ፡ ሲያልቁ
አንዱ ፡ አንዱን ፡ ሲተካው ፡ ዓለም ፡ ሲለዋወጥ
የጀግና ፡ ሰው ፡ ዙፋን ፡ መንበር ፡ ሲገለበጥ

አንተን ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሊደፍር ፡ ማን ፡ ቻለ
ሥምህ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እጅጉን ፡ አየለ
ብንሰግድልህስ ፡ አቤት ፡ ያንስብሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብርህን ፡ በዓይናችን ፡ አይተናል

አዝክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)

ፈርዖን ፡ ሊያጠፋን ፡ ኃይሉን ፡ አዘጋጀ
እንዲያው ፡ ላይሆንለት ፡ ብዙ ፡ ጦሩን ፡ ፈጀ
አንተ ፡ ግን ፡ በድንገት ፡ ደርሰህ ፡ ድል ፡ አረከው
ክብር ፡ የሚገባው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ነው

ዙፋንህ ፡ የፀና ፡ ሥምህ ፡ የገነነ
ማን ፡ አለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የተመሰገነ
ብንሰግድልህስ ፡ አቤት ፡ ያንስብሃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብርህን ፡ በዓይናችን ፡ አይተናል

አዝክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)

ሥምህን ፡ ሊያጠፉት ፡ ብዙዎች ፡ ተነሱ
ያለ ፡ የሌለውን ፡ ጦሩን ፡ አስገዝተው
ሽር ፡ ጉድ ፡ ሲሉ ፡ በምድር ፡ ጥበብ ፡ ዕውቀት
አንተ ፡ በሰራኸው ፡ ታይተው ፡ ሊነግሱበት

አስበው ፡ ሲጥሩ ፡ ከላይ ፡ አየህና
ክብርህስ ፡ ሲነካ ፡ መቼ ፡ ትውድና
ክንድህን ፡ ዘርግተህ ፡ ገለባበጥካቸው
እንደ ፡ ምድር ፡ ትቢያ ፡ በነነ ፡ ሥማቸው

አዝክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)