ከአንተ ፡ ጋራ (Kante Gara) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

አዝከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

የማይሸከሙት ፡ ለሰው ፡ የማይነግሩት
ወይ ፡ በሆድ ፡ ደብቀው ፡ የማያባብሉት
ሥጋት ፡ የማይገፋው ፡ የዚህ ፡ ምድር ፡ ጣጣ
ትንሹን ፡ ሲሸኙት ፡ ትልቁ ፡ ሲመጣ
አለፍኩት ፡ ሁሉንም ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
አቀበት ፡ ቁልቁለት ፡ ሜዳና ፡ ተራራ
ስወድቅ ፡ ያረሳኸኝ ፡ ስደክም ፡ ያነሳኸኝ
በዚች ፡ አጭር ፡ ዕድሜ ፡ ስንቱን ፡ አሳለፍከኝ

አዝከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ መውረድና ፡ መውጣት
ነፍሴን ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ እያንከራተታት
አቅም ፡ አጣሁ ፡ ብዬ ፡ ጉልበቴ ፡ ሲከዳኝ
ስጮህ ፡ ሳለቃቅስ ፡ ፈልጌ ፡ የሚረዳኝ
በእኩለ ፡ ሌሊት ፡ የመጣኸው ፡ ጌታ
ደግመህ ፡ አስታጠከኝ ፡ ጉልበቴ ፡ ሲፈታ
እቀኝልሃለሁ ፡ ክብር ፡ ይሁንልሕ
በምንም ፡ በማንም ፡ እኔስ ፡ አልለውጥህ

አዝከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

ከእንግዲህስ ፡ አይሆንም ፡ ብዬ ፡ የዘጋሁት
አምርሬ ፡ አልቅሼ ፡ አፈር ፡ ያለበስኩት
ተስፋ ፡ የሌለበት ፡ የሞተው ፡ ነገሬ
ልረሳው ፡ ስሞክር ፡ በጊዜ ፡ ቀብሬ
አንተ ፡ ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ ስታልፍበት
በሞት ፡ ፈንታ ፡ ሕይወት ፡ ብለህ ፡ ስታዝበት
የሞተው ፡ ተነስቶ ፡ ሲሄድ ፡ አይቻለሁ
ለተዓምራትህ ፡ ምስክር ፡ ሆናለሁ

አዝከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)