እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ (Egziabhier Bewenet Lemiwedu) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ
እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ
እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን (፬x)

በምድር ፡ ሰልፍ ፡ ሲያይል ፡ ሲበረታ
ያመኑትም ፡ ቃልኪዳኑ ፡ ሲፈታ
መውጫው ፡ ጠፍቶ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨላልም
መባረኪያው ፡ ዘመኑ ፡ ሲረዝም
ጌታን ፡ ታምኖ ፡ በአንዳች ፡ ሳይጨነቅ
በወጀቡ ፡ ፈርቶ ፡ ስፍራን ፡ ሳይለቅ
ማን ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ያረፈ
መከራውን ፡ በደስታ ፡ ያለፈ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ
እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ
እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን
እናምናለን ፡ ይሄን ፡ እናምናለን (፫x)

በአንበሶች ፡ ጉድጓድ ፡ መጣል ፡ መርጦ
የአንብን ፡ ማስፈራራት ፡ ረግጦ
ከልቡ ፡ ነው ፡ ለአምላክ ፡ ያደረሰው
ብርቱ ፡ ነፋስ ፡ ያላንገዳገደው
አልበላው ፡ አውሬው ፡ አንደዋዛ
በክብሩ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ ተገዛ
ቢመስል ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ የጣለው
የሚሆነው ፡ ሁሉም ፡ ለበጐ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ
እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ
እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን (፪x)
እንሰብካለን ፡ ይሄን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ቢያሰለችም ፡ የምድር ፡ ውጣ ፡ ውረድ
ሌላው ፡ ሲከብር ፡ አንተ ፡ ብትዋረድ
ብርሃኑ ፡ ቶሎ ፡ ቢመሽብህ
የታመንከው ፡ ድንገት ፡ ቢርቅብህ
ያስብሃል ፡ ጌታ ፡ በሞገሱ
አካሎችህ ፡ መከራ ፡ እስኪረሱ
አትከፋ ፡ በአምላክ ፡ ፀጋ ፡ ቻለው
አይጥልህም ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ
እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ
እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን
እንሰብካለን ፡ ይሄን ፡ እንሰብካለን
እናምናለን ፡ ይሄን ፡ እናምናለን (፪x)