በአንተ ፡ ብርታት (Bante Bertat) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

እንዴት ፡ አልፈዋለሁ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ
ያልኩት ፡ መከራዬ ፡ አሃሃ ፡ አሃሃ
እንደ ፡ ጠዋት ፡ ጤዛ ፡ አሃሃ ፡ አሃሃ
በነነ ፡ ከላዬ (፪x)

የሚያስፈራራኝ ፡ ኦሆ ፡ ከእግሬ ፡ ወደቀ
እንተ ፡ ስትመጣ ፡ ጌታ ፡ ስፍራ ፡ ለቀቀ ፡ እኮ
አንተ ፡ ከሰማይ ፡ አሃ ፡ አንዴ ፡ ካዘዝከው
የማይደነግጥ ፡ ኦሆ ፡ የማይወድቅ ፡ ማን ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ምህረትህን ፡ እያሰብኩ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እያለኝ (፪x)
መከራዬን ፡ እረሳሁ ፡ ጌታ ፡ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፡ ፀጥ ፡ አለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ባሕርም ፡ ተከፈለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
አልችለውም ፡ ያልኩት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ወድቆልኝ ፡ አየሁት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት

የሥጋት ፡ መንገዴን ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ
የነፍሴን ፡ ሰቆቃ ፡ አሃሃ ፡ አሃሃ
ዛሬ ፡ ተረት ፡ ሆነ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ
ለቅሶዬም ፡ አበቃ (፪x)
እኔም ፡ በቀኑ ፡ ተራ ፡ ደረሰኝ
በክቡር ፡ እጅህ ፡ ጌታ ፡ ክቡር ፡ አረከኝ
ያሰፈራራኝን ፡ ኦሆ ፡ አስፈራራኸው
በምህረትህ ፡ ልቤ ፡ ደስ ፡ አለው (፪x)

አዝ፦ ምህረትህን ፡ እያሰብኩ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እያለኝ (፪x)
መከራዬን ፡ እረሳሁ ፡ ጌታ ፡ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፡ ፀጥ ፡ አለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ባሕርም ፡ ተከፈለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
አልችለውም ፡ ያልኩት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ወድቆልኝ ፡ አየሁት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት

በእኩለ ፡ ሌሊት ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ
ባስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ አሃሃ ፡ አሃሃ
ማንም ፡ በሌለበት ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ
ቢጮሁ ፡ የሚሰማ (፪x)
ድንገት ፡ ተገልጠህ ፡ ኦሆ ፡ ብርሃን ፡ ስትሆነኝ
አስታውሳለሁ ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ ስታደርገኝ
እያሰብኩትም ፡ ኦሆ ፡ ቸርነትህን ፡ አሃ
ዘምረዋለሁ ፡ አሃ ፡ ምህረትህን (፪x)

አዝ፦ ምህረትህን ፡ እያሰብኩ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እያለኝ (፪x)
መከራዬን ፡ እረሳሁ ፡ ጌታ ፡ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፡ ፀጥ ፡ አለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ባሕርም ፡ ተከፈለ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
አልችለውም ፡ ያልኩት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
ወድቆልኝ ፡ አየሁት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
በአንተ ፡ ብርታት ፡ አምላኬ ፡ በአንተ ፡ ብርታት