አንተን ፡ አደንቃለሁ (Anten Adenqalehu) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(3)

ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ
(Wetmedu Tesebro Ameletkugn)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

ሰማያትን ፡ ሳይ ፡ ከዋክብትን
የፀሐይ ፡ ድምቀት ፡ ግሩም ፡ ፍጥረትህ
ምድርን ፡ ወብ ፡ አድርገህ ፡ ማበጃጀትህ
አይጠገብም ፡ አቤት ፡ ጥበብህ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
ለአንተ ፡ እዘምራለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ

አእዋፍ ፡ በዛፎች ፡ ላይ ፡ ተደላድለው ፡ ሲያርፉ
በማለዳ ፡ መዝሙር ፡ ሌሊቱን ፡ ሲገልጡ
ብሩህ ፡ ልዩ ፡ ተስፋ ፡ ጥርት ፡ ባለው ፡ ሰማይ
ትናንት ፡ ትናንት ፡ አልፎ ፡ አዲስ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ ላይ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ

የፍጥረት ፡ ቀለም ፡ ድብቅ ፡ ውበቱ
የሰማይ ፡ ርቀት ፡ የምድር ፡ ስፋቱ
ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ቤት ፡ ለሰው ፡ መቆያ
ጌታ ፡ ያዘጋጀህ ፡ መልካም ፡ ማደሪያ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ስምረትን ፡ እያየሁ

አድማስ ፡ ከሩቅ ፡ ሆኖ ፡ ፍጥረትን ፡ ሲታዘብ
ደመና ፡ ከሰማይ ፡ አውቆ ፡ ሲሰበሰብ
በዶፍ ፡ ዝናብ ፡ መሃል ፡ መብረቅ ፡ ሲያስተጋብ
ፍጥረት ፡ ቤቱን ፡ አውቆ ፡ በስፍራው ፡ ሲገባ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ

ጊዜ ፡ ጊዜን ፡ ሲወልድ ፡ ወቅቱ ፡ ሲለዋወጥ
መልካም ፡ ፍሬ ፡ አበባ ፡ አዲስ ፡ ዘር ፡ ሲገለጥ
ጭጋጉ ፡ ደመናው ፡ በድንገት ፡ ተገፎ
ፀሐይ ፡ ስትፈነጥቅ ፡ ወቅቱ ፡ በወቅት ፡ አልፎ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ

በውድቅት ፡ ሌሊት ፡ ታይቶ ፡ የማይጠገብ
ከዋክብት ፡ ሲያበሩ ፡ ግርማቸው ፡ ሲነበብ
ሰማይ ፡ እንደ ፡ ድንኳን ፡ አምሮ ፡ ተዘርግቶ
እንዴት ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ ማየት ፡ ምድርን ፡ ሞልቶ

አዝአንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ
ለአንተ ፡ ዘምራለሁ (፪x) ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ ሰማይን ፡ እያየሁ

ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥምህ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ።
እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ?
ሃሌሉያ!