From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የአምላኬን ፡ ቤት ፡ ጠላት ፡ ሲወርሰው
ሰውም ፡ ለራሱ ፡ መኖር ፡ ሲመቸው
ጠባቂው ፡ ሸሽቶ ፡ ሁሉም ፡ ሲተኛ
መንጋው ፡ ሲበተን ፡ ጠፍቶ ፡ እረኛ
አንጀቴን ፡ ልሰር ፡ ምግብ ፡ አልብላ
ነግ ፡ ይሆናል ፡ ፍርዱ ፡ በኋላ
የአምላኬ ፡ ባሮች ፡ አስኪ ፡ ተነሱ
ለፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ኑና ፡ አልቅሱ
ልመለስ ፡ ልግባ ፡ ወደ ፡ እልፍኜ
ልንቃና ፡ ልማልድ ፡ ተረድቼ
የደከምኩ ፡ ያረጀሁ ፡ ቢመስለም
በአምላኬ ፡ እኔስ ፡ተስፋ ፡ አልቆርጥም
ዓይኖቼ ፡ ፈዘው ፡ በቅጡ ፡ ሳላይ
ጠላት ፡ ሲሳሳቅ ፡ በአምላኬ ፡ ቤት ፡ ላይ
ከተኛሁበት ፡ ድንገት ፡ ስነቃ
ቅናቱ ፡ በላኝ ፡ ሆነኝ ፡ ሰቆቃ
ጉልበቴን ፡ ጠላት ፡ በልቶት ፡ ቢስቅም
መውደቄን ፡ ሰምቶ ፡ ቢጠቋቆምም
ወድቄ ፡ አልቀርም ፡ ደግሞ ፡ እነሳለሁ
የአምላኬን ፡ ቅጥሩን ፡ አሳምራለሁ
አዝ
ልመለስ
ማን ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል ፡ ሳያንሰራራ
የጠላቶቹን ፡ ጡጫ ፡ እንደፈራ
ባለቀ ፡ ስአት ፡ መድረስ ፡ የሚያውቀው
ታማኙ ፡ አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
የጠላቱን ፡ ቤት ፡ መትቶ ፡ ያፈርሳል
የእርሱ ፡ የሆኑትን ፡ ጌታ ፡ ያጠራል
ጸሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይጐበኘኛል
የሱስን ፡ ይዤ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
አዝ
ልመለስ
በአባቴ ፡ ቤት ፡ ሸቀጡ ፡ በዝቶ
ሁሉም ፡ ሊነግድ ፡ ያለውን ፡ አምጥቶ
መደቡን ፡ ሰርቶ ፡ ሰው ፡ ቢመቻችም
ኢየሱስ ፡ ይሄንን ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ አያይም
ጌታ ፡ ጅራፉን ፡ ይዞ ፡ ይነሳል
የቤቱን ፡ ጉድፍ ፡ ጠርጐ ፡ ይስወጣል
የሳቀ ፡ ጠላት ፡ በተራው ፡ ያፍራል
የክብሩ ፡ ቤት ፡ ግን ፡ ገና ፡ ያበራል
አዝ
ልመለስ
|