Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Tamagneneteh Bezu Mehereteh Lenie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ ርዕስ ታማኝነትህ ብዙ አልበም ልባርከው ጌታዬን

ታማኝነትህ ብዙ ምህረትህ ለልጅ ልጅ ነው አንተን ተስፋ አድርጐ ያፈረ ሰው ማን ነው ሁሉንም በስዓቱ ውብ አድርገህ ትሰራለህ አማካሪ አትፈልግም ብቻህን ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

በመከራ ቀን ስምህን ጠርቶ ማን ከቶ አፍሮ ያውቃል ዓይንህ ግሩም ነው በሰማይ ምስኪኑን ይመለከታል ታማኝነትህ የበዛ ምህረትህ ወደር የሌለው አንተን ተስፋ ላደረጉ እርግማኑ በረከት ነው

አዝ ታማኝነትህ ብዙ ምህረትህ ለልጅ ልጅ ነው አንተን ተስፋ አድርጐ ያፈረ ሰው ማን ነው ሁሉንም በስዓቱ ውብ አድርገህ ትሰራለህ አማካሪ አትፈልግም ብቻህን ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ታላቅ ተራራ በስምህ ደልዳላ ሜዳ ይሆናል ማዕበል ቃልህን ሰምቶ ፈጥኖ ያተዘዝልሃል ህዝብህን በምድረበዳ መናን መመገብ ታውቃለህ ቃልህን ለሚጠብቁ መች አንተ ታሳፍራለህ

አዝ ታማኝነትህ ብዙ ምህረትህ ለልጅ ልጅ ነው አንተን ተስፋ አድርጐ ያፈረ ሰው ማን ነው ሁሉንም በስዓቱ ውብ አድርገህ ትሰራለህ አማካሪ አትፈልግም ብቻህን ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ደካማው ጉልበቱ በአንተ ኃይሉ እንደንስር ታደሰ ሃያሉ ሞገስህን ሲያይ ወኔው ሃሞቱ ፈሰሰ ብላቴናው ግን በሥምህ ወንጭፍ ጠጠሩን ሰንዝሮ አየሁ ጠላቱ በቅጽበት በአደባባይ ተዘርሮ

አዝ ታማኝነትህ ብዙ ምህረትህ ለልጅ ልጅ ነው አንተን ተስፋ አድርጐ ያፈረ ሰው ማን ነው ሁሉንም በስዓቱ ውብ አድርገህ ትሰራለህ አማካሪ አትፈልግም ብቻህን ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ሰማይን ምድርን ስትራ ማን ቀርቦ አንተን አማክሯል ኤልሻዳይ ጌታ መሆንህን ፍጥረት ሁሉ ይመሰክራል ብቻህን ለዘለዓለም ጸንተህ በዙፋንህ ላይ ነህ አንተን ታምኜ እስከዛሬ ማድጋዬ መች ጐደለ

አዝ ታማኝነትህ ብዙ ምህረትህ ለልጅ ልጅ ነው አንተን ተስፋ አድርጐ ያፈረ ሰው ማን ነው ሁሉንም በስዓቱ ውብ አድርገህ ትሰራለህ አማካሪ አትፈልግም ብቻህን ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)