ሥልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (Seltan Yeante Gietayie Hoy) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(2)

ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
(Lebarkew Gietayien Lebarkew)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፈረ
ተማምኖብህ ፡ ማን ፡ ከሰረ
የተዘጋውን ፡ ትከፍታለህ
የታሰረውን ፡ ትፈታለህ
የታመመውን ፡ ታድናለህ
የሞተውን ፡ ታስነሳለህ
(ስልጣን ፡ ያንተ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ) (፪x)

ባሕር ፡ መክፈል ፡ ትችላለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
በር ፡ ሲዘጋ ፡ ትመጣለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
የችግረኛውን ፡ ጩኸት ፡ የምትሰማ ፡
የክፉ ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ ፡
እስከዛሬስ ፡ ማንን ፡ ጥለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
(ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ) (፬x)

አዝ
አንተን ፡ ጠርቶ

መርከቢቱ ፡ ስትናወጥ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
ልብም ፡ ሲርድ፡ ሲንቀጠቀጥ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
በድንገት ፡ ብቅ ፡ ብለህ ፡ ማዕበሉን ፡ ገሰጽከው
ለአምላክነትህ ፡ ኢየሱስ ፡ ፍጥረት ፡ ምስክር ፡ ነው
እኛንም ፡ ከሕይወት ፡ ማዕበል ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አሳረፍከን ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
(ስንት ፡ ጊዜ ፡ እረዳኸን ፡ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አሳረፍከን) (፪x)

አዝ
አንተን ፡ ጠርቶ

የሞተው ፡ ሲታዘዝልህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
ታላቁ ፡ ሰው ፡ ሲሰግድልህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
በዝች ፡ አጭር ፡ ዕድሜ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ አይተናል
ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ፍጥረት ፡ ለአንተ ፡ ይገዛል
ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
ለሚያምኑበት ፡ የሚያኮራ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ
(ለሚያምኑበት ፡ የሚያኮራ) (፬x)

አዝ
አንተን ፡ ጠርቶ