Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Salwedeh Yewededkegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ ርዕስ ሳልወድህ የወደድከኝ አልበም ልባርከው ጌታዬን ልባርከ

ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው (ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን ላሞጋግሰው) (፪x)

ኃጢአተኛ ሳለሁ ጽድቅ የማይገባኝ መርገሜን ወሰደው ኢየሱስ በደሙ አነጻኝ የከሰሰኝ ጠላት እግሬ ስር ወደቀ በረሃው ሕይወቴ ምንጭን አፈለቀ

አዝ ሳልወድህ የወደድከኝ...

ለዚህ የሚያበቃ ጽድቅ እንኳን ሳይኖረኝ በሰማዩ ስፍራ በቀኙ እንዲሁ አከበረኝ ምህረቱ ብዙ ይሄ ታላቅ ጌታ ከእኔ ጋር ሆናችሁ በዜማ አክብሩት በልልታ

አዝ ሳልወድህ የወደድከኝ...

የዕዳ ጽህፈቴን በደሙ ደምስሶ ጠላቴን በእጄ እረግጦ ሰጠኝ አሳልፎ ጽኑ ስልጣን አለኝ የአምላክ ልጅ ሆኛለሁ የፈታኝን ጌታ ተፈትቸ አከብረዋለሁ