Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Mesgana Ahahatitle

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

Artist Tesfaye Chala ርዕስምሥጋና አሃሃ አልበም ልባርከው ጌታዬን ልባርከው


ገናና የእኛ ኢየሱሱ አቻ አይገኝለት

እንደሞተ አልቀረም ከቶ አለ በሰማያት

ማን ይቃወመናል ዛሬስ በደሙ ዋጅቶናል

ትንሴኤውን ልናወራ (በገና አንስተናል) (፪x)

(ምሥጋና) (፫x) ለሆነው ገናና

(ዕልልታ) (፫x) ድል ላረገው ጌታ


ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ

የዕዳውን ጽህፈት በደሙ አስወግዶ

ምስኪን መስሎ መቶ ዲያብሎስን ቀጣ

በጨለማ ላሉ አዲስ ፀሐይ ወጣ


አዝ ገናና የእኛ እየሱስ...


ጐስቋላና ድሃ ምስኪን የህማም ሰው

ባየነውም ጊዜ ደም ግባት የሌለው

ፍቅር ኃይሉ ሆነች ድካሙ በረታ

ማንም ሳያግዘው ዲያብሎስን መታ


አዝ ገናና የእኛ ኢየሱስ...


የጣር የሰቆቃው ጩኸቱ ሲሰማ

መከራው በዝቶበት ቢመስልም ደካማ

ምድር አልቻለችም ሞትን ፈነቀለ

ተስፋ ለቆረጡ አዲስ ዘር በቀለ


አዝ ገናና የእኛ ኢየሱስ...


ስሙም ድንቅ መካር የሰላም አለቃ

ሞትና ርግማንም ስቃዩ አበቃ

ገናና ገናና ገናና ነው አሱ

በሆታ በልልታ ስሙን አሞግሱ


አዝ ገናና የስኛ ኢየሱስ...