Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Lebarkew Gietayien Lebarkew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ልባርከው ጌታዬን/የሱሴን ልባርከው (፬x) በሰማዩ ስፍራ ባረከኝ የረገጥኩትን አወረሰኝ ታዲያ ምን ይሰጣል ለጌታ እስኪ ከፍ አርጉልኝ በልልታ

1. የነገረኝን በሙሉ እስከሚያደርግልኝ ታምኖ ለክፉ ቀን መሸሸጊያ በሃሩር ጥላዬ ሆኖ ሲጠማኝ ምንጭ አፈለቀ ሲርበኝ ደግሞ አጐረሰኝ ሰው ዓይንህ ለአፈር ሲለኝ ኢየሱስ አንዴም ሳይሸሸኝ እንደበደሌ አልከፈለኝ ምህረቱ ስለእኔ በዝቷል በነፍስና በሥጋዬ በረከቱ ቤቴን ሞልቷል እንዴት ታዲያ ዝም ልበል ይህንን ሁሉ አይቼ ልስገድ ልውደቅ በግንባሬ ማደሪያው ቤቱ ገብቼ

2. በደሌ በፊቱ በዝቶ ያለቀ የሞትኩ ሲመስለኝ የጠላቴ ማስፈራራት ጩኸቱ ሲያርበደብደኝ በዘመርኩበት አንደበት ሙሾ ለመውረድ ስዳዳ የሞትን ወሬ ሰምቼ ለነፍሴ ሞትን ላረዳ ስዋከብ ከዚህ ወደዚያ ጭንቀቴን አይቶ ደረሰ የተዋጋኝን ተዋጋው እቅዱን አፈራረሰ ዛሬማ በኮረብታ ላይ ቆሜ ምሥጋና እዘምራለሁ ሰው ያደረገኝን አምላኬን በዜማ እባርካለሁ

3. በሰማያዊ በረከት በመንፈስ ባርኮ ባረከኝ የምድሩን አላጣሁም ይልቁን አትረፈረፈኝ ሳይሰለች የተሸከመኝ ቀን በቀን ቤቴን ባረከው ዓለም የነፈገችኝን ኢየሱስ እጥፍ አረገው የሱስን ብሎ ወዝ አጣ ያሉ ዛሬ ይሄው አፈሩ ጌታ ሞገሴ መሆኑን በአፋቸው መሰከሩ ወጥመድ ቢዘጋጅልኝም ኢየሱስ እየቀደመ ሕይወቴን በረከት ሞላው ደረቅ በትር ለመለመ

4. እናንተም አንደኔው ጌታ ቀን በቀን የባረካችሁ በተሰደዳችሁበት ምድር እጅግ ያበዛችሁ የገዛችሁን ኢየሱስ ከእግራችሁ ላስገዛላችሁ ጅራት ሳይሆን እንደ ቃሉ የሁሉ እራስ ያረጋችሁ እስኪ እናንተው ንገሩኝ ለኢየሱስ ምን ፡ ይከፈላል ወደር ለሌለው ምህረቱ ምን ምላሻ ምንስ ይሰጣል ከአድማስ አድማስ ባሻገር ሙገሳ ክብር ሙገሳ ይድረሰው ፍጥረት ሁሉ ይህን ጌታ በአንደበቱ ይቀድሰው