Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Keber Lehonen Gieta
አዝ:- ክበር የሆነን ጌታ ሞገስ የሆነን ጌታ ብቃት የሆነን ጌታ በጉድለታችን ፈንታ ክንዱን በዘመናችን በዓይናችን አይተነዋል መልካም እረኛ ኢየሱስ እስከዛሬ ረድቶናል
በዘመን በአመታት መሃል የሚገዳደረው የታል ብቻውን ድንቅ እየሰራ የሚኖር እንደተፈራ ለእኛም ይሄው ሞገስ ሆነን ባሕሩን ከፍሎ አሻገረን ችግራችንን እረሳነው በኢየሱስ ስንቱን አለፍን
አዝ ክበር የሆነን ጌታ
ስንቱን ተሻገርን አለፍን በምሥጋና ሆ እያልን
ስንቱስ ከእግራችን ወደቀ በኢየሱስ እየደቀቀ
ዘመን ሲያልፍ ዘመን ሲተካ ፍሬያችን አብቦ ፈካየረገጥነውን ወረስን እለት እለት አማረብን
አዝ ክበር የሆነን ጌታ
በምድረ በዳ በረሃ የሚያረካ ውኃ ሆነን አልሰለቸን የእኛ ጌታ እንደቃሉ ተለመነን በመከራ ቀን ሰቀቀን ተማምነን ስሙን ስንጠራ ደረሰልን በሰአቱ ኢየሱስ ጌታ የሚያኮራ
አዝ ክበር የሆነን ጌታ
ሸንጐ በእኛ ላይ ሲማከር ዲያብሎስ ሊያጠፋን ሲጥር ማነው ደርሶ የታደገን በመከራ መርከብ ሆነን ታሪ ይናገር ብዙ ነው ብዙ ነው እኛስ ያለፍነው ከእግራችን ስር ወድቆ ጠላት ጭንቅላቱን ረገጥነው አዝ ክበር የሆነን ጌታ