በራችንን ፡ ደጁን ፡ ዘግተን (Berachenen Dejun Zegten) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(2)

ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
(Lebarkew Gietayien Lebarkew)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

(ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ፡
ልባርከ ፡ እየሱሴን ፡ ልባርከው) (፪x)
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ ባረክኝ
የረገጥኩትን ፡ አወረሰኝ
(ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጠው ፡ ለጌታ
እስኪ ፡ ከፍ ፡ አርጉልኝ ፡ በልልታ) (፪x)

የነገረኝን ፡ በሙሉ ፡ እስከሚያደርግልኝ ፡ ታምኖ
የክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ የሆነው
ሲጠማኝ ፡ ምንጭ ፡ አፈለቀ ፡ ሲርበኝ ፡ ደግሞ ፡ አጐረሰኝ
ሰው ፡ ዓይንህ ፡ ላፈር ፡ ሲለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አንዴ ፡ ሳይሸሸኝ
እንደበደሌ ፡ አልከፈለኝ ፡ ምህረቱ ፡ ስለእኔ ፡ በዝቷል
በነፍስና ፡ በሥጋየ ፡ በረከቱ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቷል
እንዴት ፡ ታዲያ ፡ ዝም ፡ ልበል ፡ ይህንን ፡ ሁሉ ፡ አይቸ
ልስገድ ፡ ልውደቅ ፡ በግንባሬ ፡ ማደሪያው ፡ ቤቱ ፡ ገብቸ

አዝ
ልባርከ ፡ ጌታዬን

በደሌ ፡ በፊቱ ፡ በዝቶ ፡ ያለቀ ፡ የሞትኩ ፡ ሲመስለኝ
የጠላቴ ፡ ማስፈራራት ፡ ጩኸቱ ፡ ሲያርበደብደኝ
በዘመርኩበት ፡ አንደበት ፡ ሙሾ ፡ለመውረድ፡ ስዳዳ
የሞትን ፡ ወሬ ፡ ሰምቸ ፡ ለነፍሴ ፡ ሞትን ፡ ላረዳ
ስዋከብ ፡ ከዚህ ፡ ወደዚያ ፡ ጭንቀቴን ፡ አይቶ ፡ ደረሰ
የተዋጋኝን ፡ ተዋጋው ፡ እቅዱን ፡ አፈራረሰ
ዛሬማ ፡ በኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ
ሰው ፡ ያደረገኝን ፡ አምላኬን ፡ በዜማ ፡ እባርካለሁ

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን

በሰማያዊ ፡ በረከት ፡ በመንፈስ ፡ ባርኮ ፡ ባረከኝ
የምድሩንም ፡ አላጣሁም ፡ ይልቁን ፡ አትረፈረፈኝ
ሳይሰለች ፡ የተሸከመኝ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ ቤቴን ፡ ባረከው
ዓለም ፡ የነፈገችኝን ፡ ኢየሱስ ፡ እጥፍ ፡ አረገው
ኢየሱስን ፡ ብሎ ፡ ወዝ ፡ አጣ ፡ ያሉኝ ፡ዛሬ ፡ አፈሩ
ጌታ ፡ ሞገሴ ፡ መሆኑን ፡ በአፋቸው ፡ መሰከሩ
ወጥመድ ፡ ቢዘጋጂልኝም ፡ ኢየሱስ ፡ እየቀደመ
ሕይወቴን ፡ በረከት ፡ ሞላው ፡ ደረቅ ፡ በትር ፡ ለመለመ

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን

እናንተም ፡ እንደኔው ፡ ጌታ ፡ በቀን ፡ በቀን ፡ የባረካችሁ
በተሰደዳችሁበት ፡ ምድር ፡ እጅግ ፡ ያበዛችሁ
የገዛችሁን ፡ ኢየሱስ ፡ ከግራችሁ ፡ ያስገዛላችሁ
ጂራት ፡ ሳይሆን ፡ እንደቃሉ ፡ የሁሉ ፡ ራስ ፡ ያረጋችሁ
እስኪ ፡ እናንተው ፡ ንገሩኝ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምን ፡ ይከፈላል
ወደር ፡ ለሌለው ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ ምላሽ ፡ምንስ ፡ ይሰጣል
ከአድማስ ፡ እስከ ፡ አድማስ ፡ ሙገሳ ፡ክብር ፡ ሙገሳ ፡ ይድረሰው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ በአንደበቱ ፡ ይቀድሰው

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን