Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Bechawen Teamer Yemisera

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ ርዕስ ብቻውን ተዓምር የሚሰራ አልበም ልባርከው ጌታዬን ልባርከው


(ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ ችግረኛን የሚታደግ እንቆቅልሽ የሚፈታ ኢየሱስ የኛ ጌታ) (፪x)

ጠላት ሲሽቀዳደም ሊመታን በጡጫ ቅጥሩን ሰበረልን ሆነልን ማምለጫ እንናገር ብንል ብዙ እናወራለን በዝች አጭር እድሜ ምረቱን ስላየን በዝች አጭር ዘመን ማዳኑን ስላየን

አዝ ብቻውን ተዓምር...

ኃጢአታችን በዝቶ ስንባዝን በዓለም ሕይወት ሆነን የሱስ ሊያኖረን ዘለዓለም ምን እንመልሳለን ምሥጋና ሌላ በጭንቃችን ስዓት ለሆነን ከለላ (በጭንቃችን ስዓት ለሆነን ከለላ)

አዝ ብቻውን ተዓምር...

የአናብስትን አፍ ጥርስ እየሰበረ ከክብር ወደ ክብር እያሸጋገረ በደመናው አምድ ዘወትር ይመራናል ከኢየሱስ ጋር ሆነን አረ ምን ጐሎናል ከኢየሱስ ጋር ሆነን አረ ምን ጐሎናል

አዝ ብቻውን ተዓምር...

ጠላት ሲሽቀዳደም ሊመታን በጡጫ ቅጥሩን ሰበረልን ሆነልን ማምለጫ እንናገር ብንል ብዙ እናወራለን በዝች አጭር እድሜ ምረቱን ስላየን በዝች አጭር ዘመን ማዳኑን ስላየን

አዝ ብቻውን ተዓምር...