ሥምህ ፡ ይባረክ ፡ ለዘለዓለም (Semeh Yebarek Zelealem) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Lyrics.jpg


(1)

ባማረ ፡ ቅኔ
(Bamare Qenie)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 7:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)

ለቅሶውን ፡ የሚሰማው ፡ አጥቶ ፡ ከሰው ፡ ህሊና ፡ ተረስቶ
ደክሞ ፡ በዓልጋ ፡ እየማቀቀ ፡ ዕድሜው ፡ ዘመኑ ፡ አለቀ
የተባለው ፡ ያ ፡ ሰው ፡ ዛሬ ፡ ይሄው ፡ ቆሟል
አስኪ ፡ እዩት ፡ አልጋውን ፡ በትከሻው ፡ ይዟል
ይህን ፡ የአደረገው ፡ ክብሩ ፡ የገነነ
ኢየሱስ ፡ ይባረክ ፡ ደሃን ፡ የተለመነ

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)

አሳዳጅ ፡ እጅግ ፡ ጨካኝ ፡ ሰው
አገር ፡ ምድሩ ፡ ሁሉ ፡ የሚያወቀው
ጌታን ፡ እምርሮ ፡ ሚጠላ ፡ ለሕግ: ከልቡ፡ የቀና
ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ ፡ ይህን ፡ ሰው ፡ ሲነካው
ሥሙ ፡ ጳውሎስ ፡ ሆነ ፡ ከዚያ ፡ ማን ፡ ይቻለው
ወንጌልን ፡ በምድር ፡ በስልጣን ፡ ሰበከ
ጀግና ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጀግናውን ፡ ማረከ

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)

አፈር ፡ ለብሶ ፡ የሸተተ ፡ ህይወቱ፡ ኑሮው ፡ ተከተተ
አልዓዛር ፡ ወየው ፡ በቃለት ፡ ከኃጢአት ፡ ተለየ ፡ በሞት
ስትል ፡ ማሪያም ፡ አዝና ፡ እንባዋን ፡ እየዘራች
ምነው ፡ ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ ቢኖር ፡ ኖሮ ፡ እያለች
ተስፋ ፡ ቆርጣ ፡ ደክማ ፡ አልዓዛርን ፡ ጠራው
ኢየሱስ ፡ በዚያ ፡ ሲደርስ፡ የድል ፡ ብርሃን ፡ በራ

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)

በመንገድ ፡ ወድቆ ፡ ሲለምን ፡ አካሉ ፡ ሁሉ ፡ ሲባክን
ሰርቶ: ወይ: ደክሞ ፡ አይበላ
ዘመኑን ፡ ሁሉ ፡ ሲጉላላ
ቀኑ ፡ ደረሰና ፡ ኢየሱስ ፡ መጣለት
ደጋግሞ ፡ እየጮኸ ፡ ተጣራ ፡ በእምነት
የለማኙን ፡ጩኸት: ለይቶ: አደመጠ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ታሪኩን ፡ ለወጠ

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)

በሃኪም ፡ ገንዘቧን ፡ ጨርሳ
ሃፍረት ፡ እንደ ፡ ሸማ ፡ ለብሳ
ከሰው ፡ ከሃገሩ ፡ እየራቀች
አስራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ማቀቀች
የምስኪኖች ፡ ተስፋ ፡ በመንደሩ ፡ አለፈ
ሊጐበኛት ፡ ፈቅዶ ፡ ሸክሟን ፡ አሳረፈ
ኧረ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ምንስ ፡ ይመለሳል
እውነትም ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ለምስኪን ፡ ይደርሳል

አዝ፦ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ፡ ኢየሱስ/ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)