Tesfaye Chala/Bamare Qenie/Semeh Endemifes Zeyt New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ ርዕስ ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት

ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ጌታ ሆይ መልካም መዓዛ አለው ውዴ ሆይ መልካም መዓዛ አለው ጌታ ሆይ

ስምህን ጠርተን ተፈውሰናል ካለብን ደዌ ነጻ ወጥተናል ጅማታችንን ስምህ አራሰው ልባችን ሞልቷል ሃሌሉያ ነው ስለዚህ ጌታ ተመስገንልን አፍቅረንሃል ከውስጥ ከልብ ጎልማሳነታችንም ታድሷል በስምህ ብርታት ነጻ ወጥተናል

አይምሮ አርሶ ከልብም አልፎ ያለ ሁኔታ ተድላን አልብሶ የሚጣፍጠው ሥምህ ቁልፍ ነው ደናግል ለአንተ በፍቅር ናቸው ሌሊት በምሽት ከእንቅልፍ ተነስተን ስንበረከክ አንተን ፈልገን ስምህን ጠርተን እፎይ እረካን ኢየሱስ ጌታ ማን ይመስልሃል

ማድጋችንን ዘይትህ ሞላው ያንን ስምህን ታምነን ስንጠራው ባዶ ነበር ማስሮ ዕቃችን ግን አሁን በአንተ አገኘን ለጎረቤትም ተርፏል ሰላምህ ከእኛም አልፎ ከደናግልህ ኦ ምንልህ የምንሰጥህ የለንምና ከፍ ይበል ስምህ