From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘምሬ፡ስወርድ: ሰው: ጎሽ ፡ እንዲለኝ
ስሜን ፡ አክብሮ ፡ እንዲያሞግሰኝ
ፍፁም ፡ አልሻም ፡ ደምቆ ፡ መታየት
ክብርህን ፡ ጋርዶ ፡ እራስን ፡ መግለጽ
እኔ ፡ ውርንጫ : ነኝ ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እርሱን ፡ አክብሩልኝ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይሄ ፡ ነው
ኤፍታህ: ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ለክብሬ ፡ አይደለም
እርሱን ፡ ላከብር ፡ እንጂ ፡ ልዘምር ፡ ዘለዓለም
መሳሪያ ፡ ድምጼን ፡ የማዋህደው
ጌታን ፡ ላከብር ፡ ተመስገን ፡ ልለው
አይደለም ፡ ለእኔ ፡ ክብሩ ፡ ለእርሱ ፡ ነው
በሕይወቴ ፡ ውስጥ ፡ አለኝ ፡ ውለታው
ቆሜ ፡ ምዘምረው ፡ ሱስ ፡ ይዞኝ ፡ አይደለም
ፍቅሩ ፡ አሸንፎኝ ፡ ነው ፡ ማርኮኝ ፡ ለዘለዓለም
ልምድ ፡ የለኝም ፡ ነበር ፡ የግጥም ፡ የዜማ
ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ተስማማ (፪x)
ሃሳቡን ፡ ይዤ ፡ ላገለግለው
የውን ፡ ሃሳቤ ፡ የእንቅልፍ ፡ ህልሜ ፡ ነው
ከብሮ ፡ በዓይኔ ፡ ሳይ ፡ ጠግቤ ፡ እረካለው
ምግብ ፡ አልሻም ፡ ሆዴን ፡ እረሳለሁ
ጌታ ፡ ሲከብርልኝ ፡ ዝለል ፡ ያሰኘኛል
ዘምር ፡ በእልልታ ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
አመስግኜው ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ አልጠግብምና
ገና ፡ እዘምራለሁ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ እስኪመጣ
|