Tesfaye Chala/Bamare Qenie/Fiteh Endetsehay Yaberal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{Lyrics |ዘማሪ=ተስፋዬ ፡ ጫላ |Artist=Tesfaye Chala |ርዕስ=ፊትህ ፡ እንደፀሐይ ፡ ያበራል |Title=Fiteh Endetsehay Yaberal |አልበም=ባማረ ፡ ቅኔ |Album=Bamare Qenie |Volume=1 |Track=4 |Length=5:36 |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic

|Lyrics=

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል
እንደብዙ ፡ ውሆች ፡ ድምጽህም ፡ ያስፈራል
ግርማህ ፡የደመቀ ፡ ሞገስህ ፡ ልዩ ፡ ነው
እግርህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ እሰግድልህ ፡ አለሁ


አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
ሞትን ፡ ድል ፡ ያደረክ: ኃጢአትን ፡ የረታህ
ከወገን ፡ ከቋንቋ ፡ህዝቦችን ፡ የዋጀህ
ለአምላክህ ፡ መንግሥት ፡ ካህናት ፡አድርገህ
(ሰባቱን ፡ መጽሃፍት፡ ማህተም ፡ የፈታ
ውበትህ ፡ ያማረ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ) (፪x)

አዝ
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ

ምስኪን ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከበርክ
ደሃ ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ደሃን ፡ ያበለጸክ
በደዌ ፡ ተመተህ ፡ ህምሙን ፡ የፈወስክ
ኃጢአትን ፡ ለብሰህ ፡ ሃጢያኑን ፡ ያነጻህ
(ድል ነስተህ ፡ በኃይልህ ፡ ባለድል ፡ ያረከን
አንተ ፡ አትጠገብም ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን) (፪x)

አዝ

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ

ማምለጫ ፡ ቀዳዳ ፡ መሹለኪያ ፡ ሲጠፋ
ጐዳናው ፡እጅግ ፡ ጠቦ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲጋፋ
ችግር ፡ መፍታት ፡ አንተ ፡ ልማድህ ፡ ነውና
መጽሃፉን ፡ ገልጽህ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈታህ
ጌታችን ፡(ኢየሱስ) ፡ ተባረክ ፡ ባለግርማ ፡ ሞገስ
ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንገሥ

አዝ
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ













}አዬ}