Tesfaye Chala/Bamare Qenie/Bamare Qenie
ዘማሪ ተስፋዬ ጫላ ርዕስ ባማረ ቅኔ
አዝ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ሰው የማይችለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ፍፁም አላፍርም ባዳነኝ ጌታ አይቻለሁና በዐይኔ ያስጨነቀኝን ሲመታ ነገር ባይሞላ ባይሳካ ኢየሱስ ምን ይሳነዋል ከሞተው አንበሳ ሆድ ውስጥ ጣፋጭ ጣፋጭ ማር ያወጣል (፪x)
አዝ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ሰው የማይችለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
ለምን ልጐሳቆል ልዘን ለምንስ ልቆዝም በእንባ ተዓምር ያስለመደኝ አምላክ መቼ ክንዱ ደከመና በታሰርኩበት ወህኒ ውስጥ ሆ! እያልኩኝ እዘምራለሁ የጠላቶቼን ደጅ በእምነት በዝማሬ አፈርሳለሁ (፪x)
አዝ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ሰው የማይችለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
ውድቀቴን ጠላቴ ሰምቶ ከበሮ ተይዞ ሲጨፈር አምላኩ ጥሎታል ዛሬስ ተብሎ አዋጅ ሲነገር ሰው የማይጥል ጌታ አምላኬ ኃያል ክንዱን ሲዘረጋ ጠላቶቼ ሁሉ አለቁ በአንዲት የአህያ መንጋጋ (፪x)
አዝ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ሰው የማይችለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
ሰላሙን ሞልቶ አባቴ በመስቀሉ ስራ አሳረፈኝ ወደ ክብሩ ልጁም መንግሥት በታላቅ ፍቅሩ አፈለሰኝ ልጁን ለእኔ የሰጠ አምላክ ሌላ ምን ምን ይሳነዋል ባዶ ሸለቆዬ ሞልቶ ተርፎ ለአገር ሁሉ ይፈሳል (፪x)