Teodros Tadesse/Wa/Zem Alelem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዛሬ ፡ ጐህ ፡ ቀዶልኛል ዛሬ ፡ ቀን ፡ ወጥቶልኛል ዛሬ ፡ ጐህ ፡ ቀዶልኛል ፡ ቀዶልኛል ዛሬ ፡ ቀን ፡ ወጥቶልኛል ፡ ወጥቶልኛል

ጨለማው ፡ ሌሊት ፡ አልፏል ፡ ለእኔ ፡ ብርሃን ፡ ወጥቷል ፡ ብርሃን ፡ ወጥቷል ኢየሱሴ ፡ ቤቴ ፡ ገብቷል ፡ ቤቴ ፡ ገብቷል

ከወደኩበት ፡ መጥቶ ፡ ያነሳኝ ፡ የምሕረት ፡ እጁ አለቀቀኝም ፡ እንዳልጠፋበት ፡ ዛሬም ፡ ከደጁ ከነበርኩበት ፡ ነጥቆ ፡ ያወጣኝ ፡ የምሕረት ፡ እጁ አልለቀቀኝም ፡ እንዳልጠፋበት ፡ ዛሬም ፡ ከደጁ በቤቱ ፡ ተክሎኛል ፡ ለዘላለም ፡ ለዘላለም የሚያሰጋኝ ፡ የለም (2x )

አቤት ፡ አቤት ፡ ይገርመኛል አቤት ፡ አቤት ፡ ይደንቀኛል አቤት ፡ አቤት ፡ ግርም ፡ ይለኛል አቤት ፡ አቤት ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል አቤት ፡ አቤት ፡ ፍቅሩ ፡ ምሕረቱ አቤት ፡ አቤት ፡ ልጁ ፡ አድርጐኛል አቤት ፡ አቤት ፡ ትላንትናዬን ፡ አቤት ፥ አቤት ፥ ስረስቶኛል አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት አቤት

አወጣኝ ፡ ከጨለማ ፡ ከግዞት ፡ መንደር ሰው ፡ ከማይተርፍበት ፡ ከዚያ ፡ ከሞት ፡ ሰፈር እየመራ ፡ እየመራ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ወደ ፡ ተራራ ወደ ፡ ክብር ፡ ወደ ፡ ከፍታ ፡ አደረሰኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡

እዘምራለሁ ፡ ላዳነኝ እዘምራለሁ ፡ ለታደገኝ እዘምራለሁ ፡ ክብሬን ፥ ጥዬ እዘምራለሁ ፥ ለጌታዬ

ሳስበው እዚህ መድረሴ ለእኔም ተአምር ነው አቅሜ ጉልበቴ ብርታቴ እንዳልለው ከፀጋው ውጭ ትምክህት የሌለኝ በምህረቱ የቆምኩኝ ሰው ነኝ ሁሉ ከእርሱ በእርሱ ሆነ ቤቴ አሜን ሆነልኝ እረድኤቴ

ሜልኮል ብትንቀኝ ዝም አልልም ተቺ ቢበዛ ዝም አልልም አምልኮ አልተውም ዝም አልልም እንዲህ በዋዛ ዝም አልልም ኤረ እኔ አልልም ዝም አልልም እኔስ አልልም ዝም አልልም