Teodros Tadesse/Wa/Tez Tez Yilegnal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምን ፡ ጊዜም ፡ ማይረሳው ፡ ልቤ
ለእኔ ፡ ያረገው ፡ ውዴ
ብዘምረው ፡ ብዘምረው
ውለታው ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ነበርኩ ፡ እኔማ ፡ ሞቴን ፡ የናፈኩኝ
ጨለማ ፡ ወርሶት ፡ ሕይወቴን ፡ መኖር ፡ የታከተኝ
አትሞትም ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ አለኝ ፡ ከሰማይ ፡ ድምጽ ፡ መጣ
ድቅድቁ ፡ ሌሊት ፡ ነጋልኝ ፡ ለእኔም ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ
ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ኢየሱስ ፡ ችርነቱ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ በዝቷል ፡ ደግነቱ
ቢወራ ፡ ቢነገር ፡ የማይሰለቸኝ
የእርሱ ፡ ምሕረት ፡ ነው ፡ ደግፎ ፡ ያቆመኝ
እኔማ ፡ አልችልም ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል
እኔማ ፡ አልችልም ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል
 ምን ፡ ጊዜም ፡ ማይረሳው ፡ ልቤ
 ለእኔ ፡ ያረገው ፡ ውዴ
 ብዘምረው ፡ ብዘምረው
 ውለታው ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
በሰው ፡ ዓይን ፡ የማይሞላውን ፡ ሞገስን ፡ ያጠገበው
ከተዋረደ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳው
አይገርምም ፡ ቢያገለግለው ፡ ቢልለት ፡ ጐንበስ ፡ ቀና 
ምሕረቱ ፡ የገነነለት ፡ ምስክር ፡ ነውና 
ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ኢየሱስ ፡ ችርነቱ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ በዝቷል ፡ ደግነቱ
ቢወራ ፡ ቢነገር ፡ የማይሰለቸኝ
የእርሱ ፡ ምሕረት ፡ ነው ፡ ደግፎ ፡ ያቆመኝ
እኔማ ፡ አልችልም ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል
እኔማ ፡ አልችልም ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል