Teodros Tadesse/Wa/Amrolegnal Qenie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
  ማቄን ቀደህ እንባዬን አበስከው ቤቴን አየህው 
  ደረስክልኝ ለምስጋና በቃሁ እኔም እንደሰው.
   በቃ አለፈ መከራው ተረሳ ያ ሁሉ አበሳ
   እንደ ማርያም ከበሮን ሊያነሣ ልቤ ተነሳ


   ላመሥግንህ አምሮልኛል ቀኔ 
   ላዚምልህ ልቀኝ አዲስ ቅኔ (2x)


 ከእናቴ ማሕፀንማን ምሳያውቀኝ የመረጥከኝ.
  እንደናት እንዳባት በፍቅር ይዘሕ ያሳደከኝ
  ሰለቸኝ ታከተኝ ላፍታ ሳትለኝ ከቶ እስከዛሬ
  በኔ ብርታት ሳይሆን ባንተ አይደለሞይ 
     በሕይወት መኖሬ
  ዛሬም አንተው ነሕ ነገም ተሰፋዬ 
  የመጨረሻ መደምደሚያዬ 


   ላንተ ዘመኔን ብሰጥህ
   ላንተ ክብር ነው ለኔ
   ይህም ሲያንስሕ ነው አንዲህ መሆኔ
   ላንተ ከሆንኩት በላይ ገና ሆናለሁ
   ምላሽ ባይሆንም እዘምራለሁ


    እኔ ማውቀው መልካምነትህን
    ምናገረው ደግ መሆንሕን
   ሳሞካሸው ብውል ደጋግሜ
   ሡስ ሆኖብኝ ነው ገብቶ በደሜ


     ያየ ያውቀዋል የቀመሠ
    በፍቅርህ ዝናብ የረሰረሰ


    ሰው እንደሚያይ አንተ አታይም 
    እና ልቤን አየኸው 
    የስውር ጸሎቴን ዘልቀሕ ጓዳዬን 
     ገብተሕ ሰማኸው
    የማንም ባለዕዳ ኸረ አይደለሕም
      ልናገር እኔ
  ስራዬን ስትሠራው ሥታሳምረው ስላየሁ ባይኔ


   የቅርብ የምልህ ሚስጥረኛዬ
   የነፍሴ ወዳጅ ሑለንተናዬ