Teodros Tadesse/Wa/Adegedegalew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ደሞ ፡ ልቀኝ ፡ ነዉ ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ አሆ ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ
ገብቼ ፡ ለማጠን ፡ ዕጣ ፡ ወጣልኝ ፡ አሆ ፡ ተራዉ ፡ ደረሰኝ
መታደል ፡ ነዉ ፡ መታደል ፡ ይሄን ጌታ ፡ ማገልገል
መታደል ፡ ነዉ ፡ መታደል ፡ ይሄን ፡ ጌታ ፡ ማገልገል

አዝ ፡ - አደገድጋለዉ ፡ በፊቱ ፡ ልብሰ ፡ ተክኖዬን ፡ ለብሼ
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ካህን ፡ ነኝና ፡ ገባዉ ፡ ላመልከዉ ፡ መቅረዜን ፡ ለኩሼ
ተደርጎልኛል ፡ ተደርጎልኛል ፡ ዝምታ ፡ በእኔ ፡ መች ፡ ያምርብኛል
ተፈቅዶልኛል ፡ ተፈቅዶልኛል ፡ የፈሰሰዉ ፡ ደም ፡ እለፍ ፡ ብሎኛል

እንደ ፡ አቤል ፡ መሥወእት ፡ ከተቀበለልኝ ፡ የእኔንም ፡ ዝማሬ
እርሱን ፡ ደስ ፡ ካለዉ ፡ ዘመኔ ፡ ይጠቅለል ፡ ዘምሬ ፡ ዘምሬ
መዝሙር ፡ አላቆምም ፡ እስትንፋሴ ፡ እስካለች ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ
ሌላ ፡ ምን ፡ ስራ ፡ አለኝ ፡ የተፈጠርኩትስ ፡ ለዚማ ፡ አይደል ፡ ሆይ

አሆ ፡ ያርግልኝ ፡ አሆ ፡ አምልኮዬ ፡ አሆ ፡ ያለኝ ፡ ይኽዉ ፡ አሆ ፡ ይኽዉ ፡ ስጦታዬ
አሆ ፡ ያርግልኝ ፡ አሆ ፡ አምልኮዬ ፡ አሆ ፡ ያለኝ ፡ ይኽዉ ፡ አሆ ፡ ይኽዉ ፡ ዕልልታዬ
ይገባዋል ፡ እለዋለሁ ፡ በሙሉ ፡ ክብሩ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ
ይገባዋል ፡ እለዋለሁ ፡ በሞገሱ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ

ቃሉ ፡ ነግሮኛል ፡ ተከፍቷል ፡ ብሎኛል ፡ ቅዱስተ ፡ ቅዱሳን ፡ መግባት ፡ ሆኖልኛል
ቃሉ ፡ ነግሮኛል ፡ ተከፍቷል ፡ ብሎኛል ፡ ቅዱስተ ፡ ቅዱሳን ፡ መግባት ፡ ሆኖልኛል

ደሞ ፡ ልቀኝ ፡ ነዉ ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ አሆ ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ
ገብቼ ፡ ለማጠን ፡ ዕጣ ፡ ወጣልኝ ፡ አሆ ፡ ተራዉ ፡ ደረሰኝ
መታደል ፡ ነዉ ፡ መታደል ፡ ይሄን ጌታ ፡ ማገልገል
መታደል ፡ ነዉ ፡ መታደል ፡ ይሄን ፡ ጌታ ፡ ማገልገል

አዝ ፡ - አደገድጋለዉ ፡ በፊቱ ፡ ልብሰ ፡ ተክኖዬን ፡ ለብሼ
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ካህን ነኝና ፡ ገባዉ ፡ ላመልከዉ ፡ መቅረዜን ፡ ለኩሼ
ተደርጎልኛል ፡ ተደርጎልኛል ፡ ዝምታ ፡ በእኔ ፡ መች ፡ ያምርብኛል
ተፈቅዶልኛል ፡ ተፈቅዶልኛል ፡ የፈሰሰዉ ፡ ደም ፡ እለፍ ፡ ብሎኛል

ከላይ ፡ ከዓርያም ፡ በዙፋኑ ፡ ላለዉ ፡ በሱር ፡ ፀባኦቱ
ሲዘምሩ ፡ ሰማዉ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ሲሉ ፡ ዜማቸዉ ፡ ዉበቱ
ሽታዉ ፡ ያዉደኛል ፡ የአምልኮ ፡ መዓዛ ፡ ይሄ ፡ ህልዉና
ነፍስ ፡ አይቀርልኝም ፡ ወርዶ ፡ ሲሸፍ ፡ ነኝ ፡ የክብሩ ፡ ደመና

አሆ ፡ ያርግልኝ ፡ አሆ ፡ አምልኮዬ
አሆ ፡ ያለኝ ፡ ይኽዉ ፡ አሆ ፡ ይኽዉ ፡ ስጦታዬ
አሆ ፡ ያርግልኝ ፡ አሆ ፡ አምልኮዬ
አሆ ፡ ያለኝ ፡ ይኽዉ ፡ አሆ ፡ ይኽዉ ፡ ዕልልታዬ

ይገባዋል ፡ እለዋለሁ ፡ በሙሉ ፡ ክብሩ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ
ይገባዋል ፡ እለዋለሁ ፡ በሙሉ ፡ በሞገሱ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ

ቃሉ ፡ ነግሮኛል ፡ ተከፍቷል ፡ ብሎኛል ፡ ቅዱስተ ፡ ቅዱሳን ፡ መግባት ፡ ሆኖልኛል
ቃሉን ፡ ነግሮኛል ፡ ተከፍቷል ፡ ብሎኛል ፡ ቅዱስተ ፡ ቅዱሳን ፡ መግባት ፡ ሆኖልኛል