ይበልጣል (Yebeltal) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
አዝእግዚአብሔር ፡ ይበልጣል (፬x)
ጌታዬ ፡ ይበልጣል (፬x)
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ዓይን ፡ አላቸው ፡ አያዩም
አፍ ፡ አላቸው ፡ አያወሩም ፡ ስዕሎች
የእኔ ፡ ግን ፡ የሚሰማ ፡ የእኔ ፡ ግን ፡ የሚመልስ
ተወራርጄበት ፡ አላፈርኩም ፡ በእሱ
የእሳት ፡ ተገለጠ ፡ ይበልጣል ፡ ከእነሱ
ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ

የእነርሱማ ፡ ታየ ፡ አምላካችን ፡ ያሉት
ይሰማል ፡ ያየናል ፡ እያሉ ፡ ሚያመልኩት
የእኔ ፡ ግን (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲጠራ ፡ ከሰማይ
ደርሶ ፡ ያስመሰክራል ፡ እንደሌለው ፡ መሳይ
ይበልጣል (፫x) ፡ ከሁሉም
አንድ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚኖር ፡ እንደ ፡ ቃሉ

አዝእግዚአብሔር ፡ ይበልጣል (፬x)
ጌታዬ ፡ ይበልጣል (፬x)
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ዓይን ፡ አላቸው ፡ አያዩም
አፍ ፡ አላቸው ፡ አያወሩም ፡ ስዕሎች
የእኔ ፡ ግን ፡ የሚሰማ ፡ የእኔ ፡ ግን ፡ የሚመልስ
ተወራርጄበት ፡ አላፈርኩም ፡ በእሱ
የእሳት ፡ ተገለጠ ፡ ይበልጣል ፡ ከእነሱ
ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ

(ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ
ይበልጣል ፡ ከእነርሱ)

ህዝቡን ፡ ለመታደግ ፡ ከላይ ፡ ከተነሳ
አለሁኝ ፡ እያለ ፡ ጠላትም ፡ ቢያጋሳ
አምላኬ ፡ እሱ ፡ አይደነግጥም ፡ በሰራዊት ፡ ብዛት
ብቻውን ፡ ይበቃል ፡ አይፈልግም ፡ ረዳት
ከሰማይ ፡ ከአሪያም ፡ ድምጹን ፡ ያሰማና
ህዝቡን ፡ ይታደጋል ፡ ጠላትን ፡ ያሸሽና

አዝእግዚአብሔር ፡ ይበልጣል (፬x)
ጌታዬ ፡ ይበልጣል (፬x)
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ዓይን ፡ አላቸው ፡ አያዩም
አፍ ፡ አላቸው ፡ አያወሩም ፡ ስዕሎች
የእኔ ፡ ግን ፡ የሚሰማ ፡ የእኔ ፡ ግን ፡ የሚመልስ
ተወራርጄበት ፡ አላፈርኩም ፡ በእሱ
የእሳት ፡ ተገለጠ ፡ ይበልጣል ፡ ከእነሱ
ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ

(ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ
ይበልጣል ፡ ከእነርሱ)

በእርሳቸው ፡ ምድር ፡ በዳጐን ፡ ማደሪያ
በሚሰገድለት ፡ በእራሱ ፡ መሰዊያ
ሰገደ ፡ ሰግዶ ፡ በግምባሩ ፡ መሪት ፡ ላይ ፡ ተደፍቶ
እሱ ፡ እንደማይችል ፡ ለእነርሱ ፡ አመልክቶ
መስክሯል (፫x) ፡ ጣኦቱ
እጅ ፡ እግሮቹን ፡ ጥሎ ፡ ቀርቶ ፡ በደረቱ

አዝእግዚአብሔር ፡ ይበልጣል (፬x)
ጌታዬ ፡ ይበልጣል (፬x)
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ዓይን ፡ አላቸው ፡ አያዩም
አፍ ፡ አላቸው ፡ አያወሩም ፡ ስዕሎች
የእኔ ፡ ግን ፡ የሚሰማ ፡ የእኔ ፡ ግን ፡ የሚመልስ
ተወራርጄበት ፡ አላፈርኩም ፡ በእሱ
የእሳት ፡ ተገለጠ ፡ ይበልጣል ፡ ከእነሱ
ኃያል ፡ ነው ፡ ንጉሡ