ያልከው ፡ ይሁን (Yalkew Yehun) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ በእኔ ፡ ላይ (፬x)
ፍቃድህ ፡ ይፈጸም ፡ በእኔ ፡ ላይ (፬x)

ሁሉን ፡ አስረከብኩህ ፡ ሕይወቴን ፡ ሰጠሁህ
አንተ ፡ ያልከው ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ ተስማማሁ
ያለኝን ፡ ውሰደው ፡ አንተው ፡ ታይበት
የእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ የለኝም ፡ ትምክት (፪x)

ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ
ሁሉ ፡ ካንተ ፡ ነዉ (፪x)
የሆነዉ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ
ሁሉ ፡ ካንተ ፡ ነዉ (፪x)
የሆነዉ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ

ሁሉ ፡ ካንተ ፡ ባንተ ፡ ሆኖልኛልና
እኔ ፡ ለእኔ ፡ ምለው ፡ አይሆነኝምና
ፍቃድህ ፡ በጐ ፡ ነው ፡ ፍጻሜውም ፡ ደስታ
አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ ይሻለኛል ፡ ጌታ (፪x)

ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ
ሁሉ ፡ ከንተ ፡ ነዉ (፪x)
የሆነዉ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነዉ