ተመችቶኛል (Temechetognal) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
አለኝ (፫x) ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ
እኔ ፡ አለኝ (፫x) ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ ሚወራ ፡ ዛሬ
አቤት ፡ አቤት ፡ ስራው
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ
አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ
ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ
ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ
ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)

ተመችቶኛል (፫x) ፡ ደጁ ፡ ተመችቶኛል
ተመችቶኛል (፫x)

ምርጫዬ ፡ ሆኗል ፡ ከደጃፉ ፡ ስር
ግራ ፡ ቀን ፡ አላይ ፡ ምቹ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ
ቀን ፡ አይቶ ፡ አይገፋም ፡ አይለወጥም
በሁኔታዎች ፡ አይቀየርም
አለኝ ፡ ያልኩት ፡ ሲጠፋ ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ ሲከዳ
ኢየሱሴ ፡ ብቻውን ፡ ያለአጋዥ ፡ ረዳኝ

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ
አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ
ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ
ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ
ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)

እኔስ (፪x) ፡ ያረፍኩት ፡ የተደላደልኩት
ሸክሜን ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ የሄድኩት
ቀንበሬን ፡ ሰብሮታል ፡ የምን ፡ አንገት ፡ መድፋት
መንፈሱ ፡ ሲረዳኝ ፡ ሲሆንልኝ ፡ ስኬት
ከእንግዲህ ፡ ዓለመለስ ፡ እሄዳለሁ ፡ ወደፊት
ምርጫዬ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ የዳንኩበት ፡ እውነት

አውጥቶ ፡ አይጥልም ፡ ሁሌ ፡ ይሸከማል
አያዋርድም ፡ ይልቅ ፡ ያከብራል
ክፉ ፡ ተናግሮ ፡ ማስቀየም ፡ አያውቅም
የፍቅር ፡ ቃሉ ፡ ተነግሮ ፡ አያልቅ
በሚያባባል ፡ ቃሎቹ ፡ ውስጤን ፡ አሳርፎታል
ደስ ፡ የሚያሰኘው ፡ ምክሩ ፡ ደግፎ ፡ አቁሞኛል

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ በዛ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ መድህኔ
አላስችል ፡ አለኝ ፡ ላውጣ
ምላሽ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ ላውራ
ይሄ ፡ ደጉ ፡ አምላክ ፡ ደጉ
ዝም ፡ አያሰኝም ፡ ፍቅሩ
አትታዘቡኝ ፡ ልጩህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ደጁ
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x)
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x))
ተመችቶኛል ፡ ደጁ (፪x) (ተመችቶኛል (፪x))
ተመችቶኛል (፫x)