ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ (Segatie Ere Lemenie) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
ለምንስ ፡ እፈራለሁ ፡ ኧረ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ
ታዲያ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ ፡ እኮ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ

አዝ፦ አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ
ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ

ዘለዓለሜን ፡ ይዞታል ፡ ከቶ ፡ አትፍራ ፡ ብሎኛል
አሳርፎኝ ፡ በጉያው ፡ ስር ፡ ልምን ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር
በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ቀርጾኛል ፡ አበጃጅቶ ፡ ሰርቶኛል
አንተ ፡ የእኔ ፡ ብሎኛል ፡ ሥጋት ፡ የለኝ ፡ አሳርፎኛል

አዝ፦ አምላኬ/የጠራኝ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ
ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ (፪x)

የእኔ ፡ ነገር ፡ በእጁ ፡ ላይ ፡ ነው
ሊያደርገው ፡ የታመነ ፡ ነው
አላማዉም ፡ ከእንግዲህማ
ቀን ፡ ቆጥሯል ፡ እሱ ፡ ሊመጣ
በጊዜው ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ
ነገሬ ፡ በጌታ ፡ ሰምሮ
አያለሁ ፡ ፍርሃቴ ፡ ይብቃ
ቃል ፡ ወጥቷል ፡ ከቸሩ ፡ ጌታ

ቃል ፡ እያለኝ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የልጅነት ፡ ስልጣን ፡ የእኔ ፡ ነው
ወጀቡንም ፡ በድል ፡ አዘዋለሁ
አትፍራ ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
በቃ ፡ ልረፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ሳልሰጋ
የታምንኩት ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
ሁሉን ፡ ትቼ ፡ ሁሉን ፡ ለእርሱ ፡ ጥዬ
ያለፍርሃል ፡ ልኑር ፡ . (1) .

አዝ፦ የጠራኝ/አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ
ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ (፪x)