ለእኔ ፡ ነው (Lenie New) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
አዝየመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ
ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ
አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ

እንደሚታረድ ፡ በግ ፡ ዝም ፡ ያለው
ግርፋት ፡ ስቃዩ ፡ ለእኔ ፡ ነው
ሞቴን ፡ የሞተልኝ ፡ በጐልጐታ
ውርደቴን ፡ ተዋርዶ ፡ ክፉን ፡ መታ
በሕይወት ፡ አለሁኝ ፡ ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ጌታ

አዝየመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ
ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ
አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ

ክቡር ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ የከበረ
ጌታዬ ፡ ስለእኔ ፡ ራሱን ፡ ጣለ
እርቃኑን ፡ ሰቀሉት ፡ በእንጨት ፡ ላይ
ሃፍረቴን ፡ ሸፈነው ፡ እርሱ ፡ ሊታይ
ዝቅ ፡ አለ ፡ ወረደ ፡ ያ ፡ ኤልሻዳይ

አዝየመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ
ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ
አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ

ስለእኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር ፡ ስለልጁ
ነፍሱን ፡ እስከመስጠት ፡ ነበር ፡ እርሱ
የእኔን ፡ በደል ፡ ጌታ ፡ ተሸከመ
ተራራውን ፡ ወጣ ፡ ብዙ ፡ ደከመ
ያኔ ፡ ቀራንዮ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጸመ

አዝየመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x)
ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ቅሎ ፡ መሞቱ
ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ
አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ