ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ (Guyah Ser Negne) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ
ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ
ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ
ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን
አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን

በእርሱ ፡ ተማምኖ ፡ ለሚመካበት
አለልኝ ፡ ብሎ ፡ ለታመነበት
ያወጣል ፡ እንጂ ፡ ከቶ ፡ እርሱ ፡ አይጥልም
እንደሰው ፡ አይደል ፡ ፈጽሞ ፡ አይዋሽም
በእጁ ፡ ቀርጾ ፡ እሱ ፡ ለያዘው ፡ የጠበቀ ፡ ዋስትና ፡ አለው (፪x)

አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ
ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ
ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ
ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን
አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን

ከክንፍይ ፡ በታች ፡ ለተማመነ
ሌላውን ፡ ትቶ ፡ እርሱ ፡ አለኝ ፡ ላለ
ጽኑ ፡ መኩሪያ ፡ ነው ፡ የማይበገር
ሁኔታን ፡ አይቶ ፡ የማይቀየር
ጉያው ፡ አድርጐ ፡ አቅፎ ፡ ያሳልፋል
ትቶ ፡ አይሸስም ፡ ይልቅ ፡ ያቀርባል
(፪x)

አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ
ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ
ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ
ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን
አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን

ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስፈራው
ከጨለማው ፡ ገዢ ፡ ከማይራራው
ጋርዶ ፡ ሸሽጐ ፡ ነፍሴን ፡ የአዳነው
ልጁ ፡ ለሆኑት ፡ ደራሽ ፡ የሆነው
ቢደገፉት ፡ የማያሳፍር
አርፌያለሁ ፡ በእርሱ ፡ ጥላ ፡ ስር
(፪x)

አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x)
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ
ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ
ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ
ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን
አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን