ጊዜው ፡ ደረሰ (Giziew Derese) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
"የእረፍቴ ፡ የእረፍቴ ፡ ሰዓት (፫x)
እፎይ ፡ ምልበት (፪x)
ጊዜው ፡ ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ
ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ
ሊገላግለኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ
ደረሰ ፡ ጌዘው ፡ ደረሰ (፪x) ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ
ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ (፪x)"

የእረፍቴ ፡ ሰዓት ፡ እፎይ ፡ ምልበት
ምድርን ፡ ትቼ ፡ የምሄድበት
ጊዜው ፡ ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ
ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ (፫x)

አዝደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x)
ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x)

ጽዮን ፡ አገሬ ፡ የተመኘሁሽ
ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ በዐይኔ ፡ ላይሽ
ሁሉም ፡ ይጠራል ፡ ወደአምላኩ
ጊዜው ፡ ያበቃል ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ልኩ
ለእኔስ ፡ መኖሪያዬ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ
የዘለዓለም ፡ ቤቴ ፡ ሰማይ ፡ በአብ ፡ ቀኝ
እኔስ ፡ ማረፊያዬ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ
የዘለዓለም ፡ ቤቴ ፡ ሰማይ ፡ በአብ ፡ ቀኝ

ተስፋ ፡ እንደሌላቸው ፡ ምድር ፡ አፈር ፡ ማብቂያቸው
ያልፋል ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ምኞት ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ኧረፍት
ዛሬ ፡ ሰላምን ፡ ያጡ ፡ ሁሉም ፡ ወዴርሱ ፡ ይምጡ
መጻቱ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ ፡ ወገኔ ፡ ቶሎ ፡ ብለህ ፡ አምልጥ

አዝደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x)
ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x)

ፀሐይ ፡ ጨረቃ ፡ ከቶ ፡ የሌለበት
በጉ ፡ ኢየሱስ ፡ የሚያበራበት
ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ወደሞላበት
ደርሷል ፡ ሰዓቱ ፡ የምሄድበት
በአዲሱ ፡ አገሬ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሆኜ
አመልከዋለሁ ፡ ከመጥፋት ፡ ድኜ

አዝደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x)
ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x)
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፬x)