ግን ፡ እርሱ (Gen Esu) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
የኪዳን ፡ ልጅ ፡ ኪዳን ፡ ያለው
የተስፋ ፡ ዘር ፡ ተስፋ ፡ ያለው (፪x)

አይጠፋም ፡ ይለመልማል
ገና ፡ ምድርን ፡ ይወርሳል (፪x)

የአብርሃም ፡ ዘር ፡ ብዛ ፡ ያለው
ውረስ ፡ ያለው ፡ ቃል ፡ የሰጥው
ጋሻ ፡ ሆኖት ፡ ከለላው
በባዕድ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ መራው

አዝ፦ ግን ፡ እርሱ
አይጠፋም ፡ ይለመልማል
ገና ፡ ምድርን ፡ ይወርሳል (፪x)

ከሰማያት ፡ የወረደው
የሰው ፡ ልጅን ፡ ከፍርድ ፡ ያዳነው
ጠላቶቹ ፡ እንኳን ፡ ቢዋሹ
የመረጣቸው ፡ ቢሸሹ

አዝ፦ ግን ፡ እርሱ
አይጠፋም ፡ ይለመልማል
ገና ፡ ምድርን ፡ ይወርሳል (፪x)

በህልሞቹ ፡ የተገፋው
በጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ የተጣለው
አውሬ ፡ በላው ፡ ሞቷል ፡ በቃ
ባለራዕዩ ፡ ምን ፡ ሊያመጣ

አዝ፦ ግን ፡ እርሱ
አይጠፋም ፡ ይለመልማል
ገና ፡ ምድርን ፡ ይወርሳል
(፪x)

የኪዳን ፡ ልጅ ፡ ኪዳን ፡ ያለው
የተስፋ ፡ ዘር ፡ ተስፋ ፡ ያለው
(፪x)

አዝ፦ አይጠፋም ፡ ይለመልማል
ገና ፡ ምድርን ፡ ይወርሳል (፬x)