ደሙ (Demu) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ስሬት ፡ ያለበት ፡ ፈውስ
አሮጌነትን ፡ ሽሮ ፡ የሚያደርግ ፡ አዲስ
በደልን ፡ ሊያስወግድ ፡ ፈፅሞ ፡ ኃይል ፡ ያለው
የጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ያ ፡ ክብሩ ፡ ደሙ ፡ ነው

አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ
ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ
ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ
ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

በደም ፡ የጠበቀ ፡ ቃልኪዳን ፡ ላይሻር
ሊፋቅ ፡ ሊደመሰስ ፡ ከቶ ፡ እንዳይሞከር
ስለገባው ፡ ጠላት ፡ በደም ፡ ተማምሎ
ሊገድለኝ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ጥርሶቹን ፡ አሹሎ

ወደ ፡ እኔ ፡ ሲመጣ ፡ በእራሱ ፡ ተማምሎ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በእኔ ፡ ቦታ ፡ ሆኖ
ያ ፡ የደምን ፡ ቃልኪዳን ፡ በደሙ ፡ አምክሮ
ሕይወት ፡ ሆነልኝ ፡ ነውሬን ፡ ሸፍኖ

አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ
ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ
ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ
ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

በሰሩት ፡ ኃጢያት ፡ ልክ ፡ ማሰሪያ ፡ እንዲሆን
ይሰዉ ፡ ነበረ ፡ የእንስሳቶችን ፡ ደም
አቅም ፡ ያለውማ ፡ ይሰረይለታል
መስዕዋት ፡ የሌለው ፡ እያነባ ፡ ይኖራል

አለ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት
የሚራራ ፡ ሁሌ ፡ ለልጆቹ ፡ ሕይወት
መቅረብ ፡ እንዲችሉ ፡ ፊቱ ፡ በእኩልነት
ታሪክ ፡ ቀያየረ ፡ እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዕዋት

አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ
ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ
ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ
ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

አስጠንቅቆት ፡ ነበር ፡ የሞትን ፡ መልዓክ
የእስራኤልን ፡ ሰፈር ፡ ከቶ ፡ እንዳይታወክ
የተነገረውም ፡ እንደዚህ ፡ እኮ ፡ ነው
ደንበር ፡ ላይ ፡ ካለ ፡ ትቶ ፡ እንዲያልፍ ፡ ነው

አዎ ፡ በእኔ ፡ መንደር ፡ መታወክ ፡ አይሆንም
አሳልፎ ፡ አይሰጠኝ ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም
ዛሬም ፡ ተማምኜ ፡ ኮራ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
በደም ፡ ነው ፡ የገዛኝ ፡ ዋጋዬ ፡ ውድ ፡ ነው

አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ
ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ
ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ
ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፬x)