በተዓምራትህ (Betamerateh) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 3.jpg


(3)

የደም ፡ ኪዳን
(Yedem Kidan)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

 
በተዓምራትህ ፡ እየተገረምኩ
በተዓምራትህ ፡ እየተደነቅኩ
ዛሬም ፡ ላመልክህ/ላለነግስህ ፡ መቅደስህ ፡ ገባሁኝ (፪x)

አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ
ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ
ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ
ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x)

ሁልጊዜ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስትሰራ
ተነግሮ ፡ ተነግሮ ፡ አያልቅም ፡ ሥራህ ፡ ቢወራ (፪x)

ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ ትሆናለህ ፡ ልዩ
ተዓምር ፡ ስትሰራ ፡ ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ አዩ (፪x)

በአንደኛው (፪x) ፡ ስገረም ፡ ሌላኛው ፡ ሲመጣ
የአምላኬ ፡ የአድራጐቱ ፡ ብዛት ፡ ከውስጤ ፡ ሳይወጣ (፪x)

የአሰራሩ ፡ ሚስጥር ፡ ለእራሴ ፡ ሳይገባኝ
በኃያልነቱ ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ መራኝ (፪x)

አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ
ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ
ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ
ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x)

ከፈተው ፡ ከፈተው ፡ አፌንም ፡ እንዳመሰግነው
አስችሎኝ ፡ እንዲሁ ፡ እንዳልቀመጥ ፡ ምክንያቴን ፡ አበዛው (፪x)

ብዙ ፡ እያደረገ ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ አቆመኝ
በብቃቴ ፡ ሳይሆን ፡ በተዐምሩ ፡ አኖረኝ (፪x)

አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ
ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ
ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ
ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x)