From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አንተ ፡ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ፡ ሂድ (፮x)
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
ጉልበት ፡ ዝሎ ፡ አቅም ፡ ሲከዳ
ተስፋ ፡ አትቁረጥ ፡ ዐይንህን ፡ አንሳ
ድካምህን ፡ ለእርሱ ፡ ንገረው
ይረዳሃል ፡ የታመነ ፡ ነው
ሰውን ፡ ጥሎ ፡ ፈጽሞ ፡ አያውቅም
እዛው ፡ ሆነህ ፡ ጠብቀህ ፡ ዛሬም
ሊጐበኝህ ፡ እርሱ ፡ ሲመጣ
ምርጫ ፡ አትውሰድ ፡ ከቶ ፡ እንዳያጣህ
አዝ፦ አንተ ፡ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ፡ ሂድ (፮x)
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
አየለብኝ ፡ ወጀቡ ፡ በእኔ
ግራ ፡ ገባኝ ፡ ዛለ ፡ ጉልበቴ
አቅም ፡ አጣሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ በቃ
ጌታን ፡ ብዬ ፡ ምንስ ፡ ሊመጣ
የምታየው ፡ ተስፋ ፡ አስቆራጭ
የምጸማው ፡ ፍፁም ፡ ማይመች
ግድ ፡ የለህም ፡ ምጻቱ ፡ ቀርቦ
አትመለሰ ፡ ግባ ፡ በቶሎ
አዝ፦ አንተ ፡ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ፡ ሂድ (፮x)
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
የሙሽራው ፡ መምጫው ፡ ቀርቧል
ሩቅ ፡ አይደለም ፡ ከበርህ ፡ ደርሷል
ያለ ፡ ጊዜህ ፡ ዘይት ፡ ጨርሰህ
እንዳያጣህ ፡ ከደጃፍ ፡ ወጥተህ
ይልቅ ፡ ንቃ ፡ ይሙላ ፡ ዘይትህ
የመክበሪያ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓትህ
ልትደምቅ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
አይደነጋግዝ ፡ መብራትህ ፡ ይብራ
አዝ፦ አንተ ፡ ግን (፮x)
እስከፍጻሜው ፡ ሂድ (፮x)
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
ይመጣል ፡ ሊያሳርፍህ ፡ ተግተህ ፡ በስፍራህ
ቁም ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ አለና ፡ አትድከም ፡ በርታ ፡ ጽና
|