ዘመኔን ፡ የሰጠሁት (Zemenien Yesetehut) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ዘመኔን ፡ የሰጠሁት
ጉብዝናዬን ፡ ለእርሱ ፡ ያደረኩት
አልጣለኝም ፡ አልረሳኝም
ይዞ ፡ ሲመራኝ ፡ ሲያስመልጠኝ
ሲያሻግረኝ ፡ ዛሬን ፡ አሳየኝ (፪x)
ስለዚህ ፡ ልበል ፡ ላውራው ፡ ልናገር
የደረሰልኝ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር
የተረሳውን ፡ አስታዋሽ ፡ እርሱ
ዛሬም ፡ እላለሁ ፡ የለም ፡ እንደእርሱ

ቀየረው ፡ ገብቶ ፡ በቤቴ
አንገት ፡ መድፋት ፡ ቀረ ፡ በሕይወቴ
ታማኝ ፡ ነው ፡ የምስኪን ፡ ወዳጅ
ሁሉ ፡ አለ ፡ ስለሆንኩኝ ፡ ልጅ
ሁሉ ፡ አለ ፡ ስለሆንኩኝ ፡ ልጅ
ሁሉ ፡ አለ ፡ ስለሆንኩኝ ፡ ልጅ (፪x)

ገባ ፡ ገባ ፡ ገባ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴ
አማረ ፡ በእርሱ ፡ ሕይወቴ
ተለወጠ ፡ ያ ፡ ማንነቴ
አንድ ፡ ሰው ፡ ነኝ ፡ በመድሃኒቴ (፪x)

ቀናልኝ ፡ መንገዴ ፡ የሚያዋጣውን ፡ ይዤ
ሁሉ ፡ አማረልኝ ፡ በዚህ ፡ በወዳጄ
ክብርን ፡ ሳላስበው ፡ መጣ ፡ ወደቤቴ
ተደላድያለሁ ፡ አርፌ ፡ በአባቴ

ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ወዳጄ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
አባቴ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
የጠራኝ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ

ምናገረው ፡ አለኝ ፡ ክተደረገልኝ
ቸር ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ አቆመኝ
አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ ላውራው ፡ ልመስክር
ከጌታዬ ፡ ሌላ ፡ አልውቅም ፡ ክብር

ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ወዳጄ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
አባቴ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
የጠራኝ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ
ኢየሱስ ፡ ቤቴ ፡ ሲገባ