ተወለደ (Tewelede) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ በልጁ ፡ ሊፈጸም
ራሱን ፡ ዝቅ ፡ አድርጐ ፡ ወረደ ፡ ለዓለም
በምድር ፡ ሊሰማ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ
ከድንግል ፡ ማሪያም ፡ ተወለደ ፡ ጌታ (፬x)

አዝ፦ ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)

እነሆ ፡ የምስራች ፡ እነሆ ፡ የምስራች
ዛሬ ፡ በዳዊት ፡ ከተማ
እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ
ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x)

እረኞች ፡ ለማየት ፡ እጅጉን ፡ ጓጉለት
ሰባ ፡ ሰገል ፡ መተው ፡ ወድቀው ፡ ሰገዱለት
የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ የዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ
ከአብ ፡ ሊያስታርቀን ፡ ተወለደ ፡ ኢየሱስ (፬x)

አዝ፦ ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)

መላዕክት ፡ አበሰሩ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል
ዛሬ ፡ በቤቴልሄም ፡ ወንድ ፡ ልጅ ፡ ተወልዷል
ምድር ፡ ዕልል ፡ ትበል ፡ ታሰማ ፡ ምሥጋና
ሕዝቡን ፡ የሚታደግ ፡ መሲህ ፡ መጥቷልና (፬x)

አዝ፦ ተወለደ (፬x)
ተወለደ (፬x)

እነሆ ፡ የምስራች ፡ እነሆ ፡ የምስራች
ዛሬ ፡ በዳዊት ፡ ከተማ
እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ
ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x)